ኢትዮጵያ የቶኪዮ ኦሎምፒክስ የአትሌቲክስ ተወዳዳሪዎቿን ይፋ አደረገች

የፎቶው ባለመብት, World Athletics facebook page
በቅርቡ በኔዘርላንድስ ሄንግሎ በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች ከአንድ እስከ ሶስተኛ የወጡ አሸናፊዎች በቶኪዮ ኦሎምፒክስ አገራቸውን ወክለው እንደሚወዳደሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ከ800-10 ሺህ ሜትር ባሉ ውድድሮች እንዲሁም 3000 ሜትር መሰናክልን ጨምሮ በአምስት ውድድሮች በሁለቱም ፆታ አገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶች በውጤታቸው መሰረት ተሰላፊዎቹና ተጠባባቂዎቹ ተለይተዋል።
ከቀናት በፊት በነበረው የ10 ሺህ የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ለተሰንበት ግደይከሁለት ቀናት በፊት በሲፋን ሀሰን ተሰብሮ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸናፊ መሆን ችላለች።
በዚህ በ29 ደቂቃ ከ1.03 አሸናፊ በሆነችበት ውድድር ፅጌ ገብረ ሰላማ በሁለተኝነት፣ ፀሃይ ገመቹ በሶስተኝነት አሸናፊ ሆነዋል።
በቀጣዩ የቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩት ለተሰንበት ግደይ፣ ፅጌ ገብረሰላማ፣ ፀኀይ ገመቹና በተጠባባቂነት ያለም ዘርፍ የኋላው ናቸው።
በቶኪዮ ኦሎምፒክስ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ዝርዝር
በ800 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች
- ወርቅውሃ ጌታቸው
- ሃብታም አለሙ
- ወርቅነሽ መሰለ
- ነፃነት ደስታ (ተጠባባቂ)
በ1500 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች
- ፍሬወይኒ ኃይሉ
- ድሪቤ ወልተጂ
- ለምለም ኃይሉ
- ትእግስት ከተማ (ተጠባባቂ)
በ5000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች
- ጉዳፍ ፀጋዬ
- እጅጋየሁ ታዬ
- ሰንበሬ ተፈሪ
- ፋንቱ ወርቁ (ተጠባባቂ)
በ1000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች
- ለተሰንበት ግደይ
- ፅጌ ገብረሰላማ
- ፀኃይ ገመቹ
- ያለምዘርፍ የኋላው(ተጠባባቂ)
በ3000 ሜትር መሰናክል የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች
- መቅደስ አበበ
- ሎሚ ሙለታ
- ዘርፌ ወንድማገኝ
- አገሬ በላቸው (ተጠባባቂ)
በወንዶች 10ሺህ ሜትር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አራተኛ ደረጃ የያዙ ሲሆን አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ26 ደቂቃ 49 ሰከንድ ከ51 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል።
እሱን በመከተል ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ሀጎስ ገብረህይወት ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
በ1500 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች
- ታደሰ ለሚ
- ሳሙኤል አባቱ
- ሳሙኤል ተፈራ
- መለሰ ንብረት (ተጠባባቂ)
በ5000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች
- ጌትነት ዋለ
- ንብረት መላክ
- ሚልኬሳ መንገሻ
- አዲሱ ይሁኔ(ተጠባባቂ)
በ10000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች
- ሰለሞን ባረጋ
- ዮሚፍ ቀጄልቻ
- በሪሁ አረጋዊ
- ሀጎስ ገብረህይወት (ተጠባባቂ)
በ3000 ሜትር መሰናክል የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች
- ታደሰ ታከለ
- አብርሃም ስሜ
- ኃይለማርያም አማረ
- ለሜቻ ግርማ (ተጠባባቂ)
የቶክዮ ኦሎምፒክ 2020/2021 ከሐምሌ 16- ነሐሴ 2 ድረስ ይካሄዳል።












