የግብጽ ህዝብ ቁጥር መቶ ሚሊዮን መድረሱ ተነገረ

የሰሜናዊቷ አፍሪካ አገር ህዝብ ቁጥር አንድ መቶ ሚሊዮን መድረሱ ተገለጸ።

በየአስራ ስምንት ሰከንዱ ህፃን በሚወለድባት ግብጽ ይህ ቁጥር ብዙ አያስደንቅም ተብሏል።

የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞስጠፋ ማድቦሌ የግብጽ ህዝብ ቁጥርን በፍጥነት ማደግ አስመልክቶም አገሪቱ እየገጠማት ካሉት ተግዳሮቶች መካከል ዋነኛው ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ነው ብለዋል።

በአገሪቷ አመራሮች ዘንድ በበጎ ያልታየው ይህ ቁጥር ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲሰም በበኩላቸው ባልተጠበቀ መልኩ ከሽብርተኝነት ስጋት ጋር አመሳስለውታል።

በቅርቡም ባለስልጣናቱ ሕዝቡ ጥቂት ልጆች እንዲወልድ የሚያበረታቱ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመራቸውም ተዘግቧል።

የግብፅ የህዝብ ቁጥርን እድገት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ነው የሚሉት ተንታኞች በተለይም ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ከፍተኛ የሆነ መጨመርን አሳይቷል ይላሉ።

በጎርጎሳውያኑ 1990 የሃገሪቱ የህዝብ ቁጥር 57 ሚሊዮን ነበር።