የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አረፉ

የፎቶው ባለመብት, PHILL MAGAKOE
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓመት በሞት ተለዩ።
ዚምባብዌ ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የመጀመሪያው መሪ የሆኑት ሙጋቤ፤ ባደረባቸው ህመም ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ሙጋቤ ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ሲንጋፖር በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተከታተሉ ነበር።
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2017 ላይ የዚምባብዌ መከላከያ ኃይል፤ ሮበርት ሙጋቤ ለሦስት አሥርት ዓመታት ይዘውት ከነበረው መንበረ ሥልጣን ማስነሳቱ ይታወሳል።
በ1980 በዚምባብዌ የተካሄደውን የመጀመሪያ ምርጫ አሸንፈው ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የነበሩት ሙጋቤ፤ 1987 ላይ ፕሬዘዳንት ሆነዋል።
የአገሪቱ የትምህርት ሚንስትር ጸኃፊ ፋዲዛይ ማሀሬ "ነፍስዎትን በገነት ያኑራት" ብለው በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
ሙጋቤ የተወለዱት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1924 ነበር።
ከእንጨት ሠሪ ቤተሰብ የተገኙት ሙጋቤ፤ በካቶሊክ የሚሽነሪ ትምህርት ቤት ነበር ትምህርታቸውን የተከታተሉት።












