ከአዲስ አበባ ናይሮቢ በመብረር ላይ የነበረው ET302 ተከሰከሰ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ዛሬ እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 የበረራ ቁጥር ET302 መከስከሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በትዊተር ገፁ አስታውቋል።

አውሮፕላኑ 149 ሰዎችን እንዲሁም 8 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ እንደነበርና ከተነሳ ከ ስድስት ደቂቃ በኋላ ግንኙነት መቋረጡን ፋና ዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአንድ ሰዓት በፊት ባወጣው የአደጋ ሪፖርት ጠዋት 2፡38 ከአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው አውሮፕላን የተከሰከሰው ደብረዘይት አካባቢ እንደሆነ አስታውቋል።

ምን ያህል ሰው ሞተ ወይም ተረፈ ስለሚለው የታወቀ ነገር እንደሌለና የተሳፋሪዎችን ማንነት የሚያጣራ የመረጃ ማእከል በመክፈት ላይ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።

እስካሁን ስለ አደጋው መንስኤ የተባለ ነገር የለም።