ኤፕሪል 2 2018, 1 ቀን በሥራ ገበታ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢህአዴግ ሊቀ መንበር ከሆኑ ከሳምንት በኋላ በሕዝብ እንደራሴዎች ፊት ቃለ መሀላ ፈጸሙ። በእለቱ ስለ ህብረትና ለውጥ ተናግረዋል።
ኤፕሪል 28 2018, 27 ቀን በሥራ ገበታ ላይ ሥልጣን ይዘው ብዙም ሳይቆይ በክልል ከተሞች እየተዘዋወሩ ነዋሪዎችን ማነጋገር ያዙ። በደቡብ ክልል ሀዋሳ ከተማ ተገኝተው የጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን ዘመን ከአስር አመት እንደማይዘል አሳውቀዋል።
ኤፕሪል 29 2018, 28 ቀን በሥራ ገበታ ላይ ከሀገር ውጪ መጀመሪያ ያቀኑት ወደ ጅቡቲ ሲሆን ከጅቡቲው አቻቸው ጋር ስለ ኢኮኖሚያዊ ትስስርና የቀጠናው ሰላም ተወያይተዋል። ኢትዮጵያውያን ታራሚዎችንም ከጅቡቲ አስፈትተዋል።
ሜይ 29 2018, 28 ቀን በሥራ ገበታ ላይ እንግሊዛዊ ዜግነት ያላቸው የግንቦት 7 መሪ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሞት ፍርዳቸው ተሽሮ ከእስር ተለቀቁ። በተለቀቁ ማግስት በብሔራዊ ቤተ መንግስት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኙ።
ሜይ 18 2018, 47 ቀን በሥራ ገበታ ላይ ከአፍሪካ ውጪ ባደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝት ወደ ሳውዲ አረቢያ አምርተው ለሁለት ቀናት በሁለትዮሽ ጉዳዮች እንዲሁም በአለም አቀፍ ሁነቶት ከልዑል መሀመድ ቢን ሰልማን አብዱል ጋር ተወያይተዋል። ጉብኝታቸውን ተከትሎ ከ1000 በላይ ኢትዮጵያውያን ታራሚዎች ከእስር ተለቀዋል።
ጁን 4 2018, 64 ቀን በሥራ ገበታ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለስድስት ወራት የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳል ከተባለበት ግዜ ሁለት ወራት ቀድሞ የተነሳው በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት በመስፈኑ ነው ተብሏል።
ጁን 6 2018, 66 ቀን በሥራ ገበታ ላይ ገዢው ፓርቲ በመንግስት ባለቤትነት ስር የነበሩትን ቴሌ ኮሙኑኬሽንና አየር መንገድን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች በከፊል ለመሸጥ መወሰኑ ዋነኛ የፖሊሲ ለውጥ ነበር። በሥራ አስፈፃሚው መግለጫ መሰረት ይህ ውሳኔ ያስፈለገው የሀገሪቱን ፈጣን እድገት ለማስቀጠል ነው። በዚሁ ዕለት ነበር የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ለመተግበር የተወሰነው።
ጁን 7 2018, 67 ቀን በሥራ ገበታ ላይ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በጀነራል ሳሞራ የኑስ ምትክ ጀነራል ሰአረ መኮንንን የመከላከያ አዛዥ አድርገዋል። የፀጥታና ደህንነት ኃላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋም በአቶ አደም መሀመድ ተተክተዋል።
ጁን 9 2018, 69 ቀን በሥራ ገበታ ላይ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይ አህመድ የኡጋንዳን ከፍተኛውን ሜዳሊያ ተሸልመው በሚቀጥለው ቀን ወደ ግብፅ ተጉዘው የግብፅ አቻቸውን ያገኙ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱም ከግብፅ የተለቀቁ ታራሚዎችን እንዲሁም የኦነግ አመራር አባላትን ይዘው ተመልሰዋል።
ጁን 18 2018, 78 ቀን በሥራ ገበታ ላይ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ መንግሥት የፖለቲከኛ እስረኞችን ያሰቃይ እንደነበር ይህም ህገ መንግስታዊ እንዳልሆነ ገልፀዋል። ‘ ማሰርና ማሰቃየት ኢ-ህገመንግስታዊ ነው። ሽብርተኝነት ህገ መንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረግ እርምጃንም ይጨምራል' ብለዋል።
ጁን 23 2018, 83 ቀን በሥራ ገበታ ላይ ቅዳሜ ሰኔ 16 በመስቀል አደባባይ ለድጋፍ በወጡ ሰልፈኞች ላይ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ሁለት ሰዎች ሞተዋል። ከፍንዳታው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቃቱ የእለቱን ስሜት ለማጠልሸት የተቀነባበረ ነው ብለዋል።
ጁን 26 2018, 86 ቀን በሥራ ገበታ ላይ የኤርትራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ኢትዮጵያና ኤርትላ ላለፉት 20 ዓመታት አለመግባባት ውስጥ ቆይተዋል። እንደ ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሆነ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በቅርቡ ይገናኛሉ።
ጁላይ 5 2018, 97 ቀን በሥራ ገበታ ላይ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት በሽብርተኝነት ተፈርጀው የነበሩትን ኦነግ፣ ኦብነግ እና ግንቦት 7 ሽብርተኞች አይደሉም በማለት ከሽብርተኛ ድርጅቶች ዝርዝር አውጥቷቸዋል።
ጁላይ 08 2018, 98 ቀን በሥራ ገበታ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ኤርትራ መዲና አስመራ አቅንተዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አየር ማረፊያ በመገኘት ኤርትራውያን ደግሞ በነቂስ አደባባይ ወጥተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጉብኝቱ ባለፉት ሁለት አስርታት የነበረውን ውጥረት ያረገበና በሁለቱ ሀገሮች መካከል ሰላም ስለማንሰራራቱ ምልክት ነው ተብሏል።
ቃለ መሀላ ፈጸሙ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢህአዴግ ሊቀ መንበር ከሆኑ ከሳምንት በኋላ በሕዝብ እንደራሴዎች ፊት ቃለ መሀላ ፈጸሙ። በእለቱ ስለ ህብረትና ለውጥ ተናግረዋል።
ለሥልጣን ዘመን ገደብ? ሥልጣን ይዘው ብዙም ሳይቆይ በክልል ከተሞች እየተዘዋወሩ ነዋሪዎችን ማነጋገር ያዙ። በደቡብ ክልል ሀዋሳ ከተማ ተገኝተው የጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን ዘመን ከአስር አመት እንደማይዘል አሳውቀዋል።
ወደ ጅቡቲ አቀኑ ከሀገር ውጪ መጀመሪያ ያቀኑት ወደ ጅቡቲ ሲሆን ከጅቡቲው አቻቸው ጋር ስለ ኢኮኖሚያዊ ትስስርና የቀጠናው ሰላም ተወያይተዋል። ኢትዮጵያውያን ታራሚዎችንም ከጅቡቲ አስፈትተዋል።
አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር ተለቀቁ እንግሊዛዊ ዜግነት ያላቸው የግንቦት 7 መሪ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሞት ፍርዳቸው ተሽሮ ከእስር ተለቀቁ። በተለቀቁ ማግስት በብሔራዊ ቤተ መንግስት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኙ።
ከአፍሪካ ውጪ የመጀመርያው ይፋዊ ጉብኝት ከአፍሪካ ውጪ ባደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝት ወደ ሳውዲ አረቢያ አምርተው ለሁለት ቀናት በሁለትዮሽ ጉዳዮች እንዲሁም በአለም አቀፍ ሁነቶት ከልዑል መሀመድ ቢን ሰልማን አብዱል ጋር ተወያይተዋል። ጉብኝታቸውን ተከትሎ ከ1000 በላይ ኢትዮጵያውያን ታራሚዎች ከእስር ተለቀዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለስድስት ወራት የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳል ከተባለበት ግዜ ሁለት ወራት ቀድሞ የተነሳው በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት በመስፈኑ ነው ተብሏል።
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ ገዢው ፓርቲ በመንግስት ባለቤትነት ስር የነበሩትን ቴሌ ኮሙኑኬሽንና አየር መንገድን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች በከፊል ለመሸጥ መወሰኑ ዋነኛ የፖሊሲ ለውጥ ነበር። በሥራ አስፈፃሚው መግለጫ መሰረት ይህ ውሳኔ ያስፈለገው የሀገሪቱን ፈጣን እድገት ለማስቀጠል ነው። በዚሁ ዕለት ነበር የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ለመተግበር የተወሰነው።
የወታደራዊና የደህንነት አመራሮች ስልጣን ሽግሽግ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በጀነራል ሳሞራ የኑስ ምትክ ጀነራል ሰአረ መኮንንን የመከላከያ አዛዥ አድርገዋል። የፀጥታና ደህንነት ኃላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋም በአቶ አደም መሀመድ ተተክተዋል።
ኡጋንዳ -ግብፅ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይ አህመድ የኡጋንዳን ከፍተኛውን ሜዳሊያ ተሸልመው በሚቀጥለው ቀን ወደ ግብፅ ተጉዘው የግብፅ አቻቸውን ያገኙ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱም ከግብፅ የተለቀቁ ታራሚዎችን እንዲሁም የኦነግ አመራር አባላትን ይዘው ተመልሰዋል።
መንግስት በሽብር ተግባር ጠቅላይ ሚኒሰትሩ መንግሥት የፖለቲከኛ እስረኞችን ያሰቃይ እንደነበር ይህም ህገ መንግስታዊ እንዳልሆነ ገልፀዋል። ‘ ማሰርና ማሰቃየት ኢ-ህገመንግስታዊ ነው። ሽብርተኝነት ህገ መንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረግ እርምጃንም ይጨምራል' ብለዋል።
የቦንብ ፍንዳታ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ቅዳሜ ሰኔ 16 በመስቀል አደባባይ ለድጋፍ በወጡ ሰልፈኞች ላይ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ሁለት ሰዎች ሞተዋል። ከፍንዳታው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቃቱ የእለቱን ስሜት ለማጠልሸት የተቀነባበረ ነው ብለዋል።
የኤርትራ ልዑካን በኢትዮጵያ የኤርትራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ኢትዮጵያና ኤርትላ ላለፉት 20 ዓመታት አለመግባባት ውስጥ ቆይተዋል። እንደ ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሆነ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በቅርቡ ይገናኛሉ።
አሸባሪዎች አይደሉም የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት በሽብርተኝነት ተፈርጀው የነበሩትን ኦነግ፣ ኦብነግ እና ግንቦት 7 ሽብርተኞች አይደሉም በማለት ከሽብርተኛ ድርጅቶች ዝርዝር አውጥቷቸዋል።
አስመራ ደረሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ኤርትራ መዲና አስመራ አቅንተዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አየር ማረፊያ በመገኘት ኤርትራውያን ደግሞ በነቂስ አደባባይ ወጥተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጉብኝቱ ባለፉት ሁለት አስርታት የነበረውን ውጥረት ያረገበና በሁለቱ ሀገሮች መካከል ሰላም ስለማንሰራራቱ ምልክት ነው ተብሏል።