ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ለገበያ ያቀረቡ ተፈረደባቸው
የቤኒን ፍርድ ቤት ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ሸጠዋል ያላቸውን የህክምና እቃዎች አምራች ኩባንያ ከፍተኛ አመራሮችን አሰረ።
በምዕራብ አፍሪካ ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ይገኛል።
መድሃኒቶች ሃሰተኛ ናቸው የሚባሉት ይዘዋል የተባለው ንጥረ-ነገር ሳይኖራቸው ወይም አነስተኛ ሆኖ ሲገኘ ነው።
አብዛኛውን ጊዜ ሃሰተኛ መድሃኒቶች ትክክለኛ ከሚባሉት መድሃኒቶች ጋር ተመሳሳይ ገጽታ እንዲኖራቸው ተደርጎ ይሰራል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰባቱ ግለሰቦች በቤኒን እና በቀጠናው ለሚገኙ ሀገራት ከህመም ማስታገሻዎች እሰከ ጸረ-ወባ መድሃኒቶች ድረስ በጅምላ ያከፋፈሉ ነበር።
ግለሰቦቹ የአራት ዓመት እስራት እና የ$190,000 ቅጣት ተላልፎባቸዋል።