ክብደት ለመቀነስ የሚወሰዱ ፈሳሽ ምግቦች ይጠቅማሉ? ጤናማስ ናቸው?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሼን ዋርን አርብ ዕለት ነበር ሕይወቱ ያለፈው።
በተፈጥሯዊ ምክንያት ሕይወቱ ማለፉ ተነግሯል። ግለሰቡ ክብደት በፍጥነት ለመቀነስ በሚል ለ14 ቀናት ፈሳሽ ምግብ ብቻ ሲወስድ ቆይቷል።
ከመሞቱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ "የሰኔ ወር ዕቅዴ ከጥቂት ዓመታት በፊት ወደነበርኩበት ወደዚህ የሰውነት ቅርፅ መመለስ ነው" ሲል የድሮ ፎቶን ጨምሮ ትዊተር ላይ አስፍሯል።
ከብደቱን ለመቀነስ በተደጋጋሚ ጊዜ መሞከሩን ጓደኞቹ ተናግረዋል።
ስለዚህ እነዚህ ምግቦች ምን ያህል ደኅንነታቸው የተጠበቀ ነው?
በሰውነት ላይ ያላቸው ተጽዕኖስ ምንድነው?ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ብዙ ዓይነት ፈሳሽ ምግቦች አሉ። ይህም አነስተኛ ካሎሪን በመመገብ በፍጥነት ክብደትን መቀነስ ነው። ዓይነታቸው ብዙ ነው።
ክብደትን ይቀንሳል እንዲሁም ሰውነትን ያጸዳል ብለው ቃል ከሚገቡ የፍራፍሬ እና የአትክልት ጭማቂዎች እስከ ዝቅተኛ የካሎሪ ይዘት ያለው ጭማቂዎች እና ሾርባዎች ይደርሳል።ባለሙያዎች ግን ተጠንቀቁ ይላሉ።
እነዚህን መጠቀም ከልክ ያለፈ የአመጋገብ የጤና እክሎች እንደሚያስከትሉ እና ለብዙ ሰዎችም አይስማሙም ሲሉ ይመክራሉ።
የእንግሊዙ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት (ኤንኤችኤስ) በቀን 800 ካሎሪ ማገኘት አስፈላጊ ነው የሚለውም ለተወሰኑ ሰዎች ነው። በተለይም ዓይነት 2 የስኳር በሽታን ላለባቸው እና ወፍራም ወይም በጣም ወፍራም ለሆኑ ሰዎች ነው።
ቢሳካም ተሞክሮ እና ተጠንቶ ከብዙ ድጋፍ እና የህክምና ክትትል ጋር ነው የሚመጣው። ይህ ግን በበይነ መረብ በሚገዙ ፈሳሽ ምግቦች ላይ የሚሳካው አልፎ አልፎ ነው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሌሎች የጎንዮሽ ጉዳቶች ደግሞ ራስ ምታት፣ ማዞር፣ ከፍተኛ ድካም፣ ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት ናቸው።
ብዙ ተፈጥሯዊ አሲዶችን የያዙ የፍራፍሬ ጭማቂዎች የጥርስን ኢናሜል (የጥርስ መስታወት የሚባለው ነው) ያበላሻሉ።
በቂ ካሎሪ አለመኖር የትንፋሽን ጠረንን ይቀይረዋል።በፈሳሽ ምግቦች ክብደትን በፍጥነት መቀነስ ይቻላል።
እንደ ባለሙያ ገለጻ ትልቁ ፈተና የ"ዮ-ዮ ስጋት" ነው። ይህም የምግብ አወሳሰድ ወደ መደበኛው ሲመለስ ክብደትን እንደገና የመጨመር አደጋ ማለት ነው።
አንዳንዴ ታዋቂ የሚሆን የአመጋገብ ሥርዓት "የመርዛማ አመጋገብ ባህል አካል" ነው። ለምግብ አሉታዊ አመለካከቶችን የሚያበረታታ ሲሆን ክብደት ከመቀነስ ወደ መጨመር የሚያመራ ነው ይላሉ።
የራስዎን ሰውነት ያደድምጡ፣ ወደ መሠረታዊ መርሆች ይመለሱ፣ ለአንድ ሳምንት ብቻ ሳይሆን በረዥም ጊዜ ሊደረስባቸው የሚችሉ ግቦችን ያስቀምጡ ሲሉም ይመክራሉ።
"የክብደት ሽክርክሪት"
የብሪቲሽ የሥነ-ምግብ ፋውንዴሽን ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ሳይመን ስቴንሰን እንደሚሉት "ከባድ በሆነ የምግብ መቀነስ ወይንም የካሎሪ መጠንን በመቀነስ ዘላቂ መፍትሄ አይሆንም።
የቀነስ ሚመስለን ውሃ ወይንም የዛለ ጡንቻ ነው። "ክብደት ለመቀነስ በፍጥነት እና በአጭር ጊዜ የሚደረጉ የአመጋገብ ለውጦች ለአንዳንዶች እንደ ሃሞት ጠጠር ወደ መሰሉ የጤና ችግሮችም የማምራት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
"ዶ/ር ስቴንሰን አንዳንዴ ታዋቂ የሚሆን የአመጋገብ ሥርዓት "የክብደት ሽክርክሪት" ያመጣል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።
ክብደት አንዴ መቀነስ ቀጥሎ ደግሞ መወፈር የሚያስከትል ሽክርከሪት ማለት ነው።
ይህ ደግሞ ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል። ክብደትን ለመቀነስ የተሻለው አማራጭ ብዙ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ባቄላ እና ለውዝን ጨምሮ የተመጣጠነ አመጋገብን መከተል እና ቀኑን ሙሉ አንቅስቃሴ ማድረግ የሚችሉባቸውን መንገዶች መፈለግ ነው ይላሉ።
ፈጣን "ፈሳሽ የክብደት የመቀነሻ አመጋገብ" ላይ ከማተኮር ይልቅ ያልተፈለገ ካሎሪ ያላቸውን እንደአልኮል፣ የድንች ጥብስ፣ ብስኩት እና ፈጣን ምግቦችን ከአመጋገብዎ ውስጥ ማስወገድ መፍትሔ መሆኑን ዶክተር ሪስ ይመክራሉ።
መሠረታዊ የጤና እክል ካለብዎ ይህን መሰሉን የአመጋገብ ሥርዓት ከመጀመርዎ በፊት ሐኪም ወይም የሥነ-ምግብ ባለሙያ ያነጋግሩ።
በትክክለኛው መንገድ እና ተስማሚ በሆኑ ሰዎች ላይ ፈሳሽ ምግቦች ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ። ለብዙ ሰዎች ግን ለመተግበር በጣም አስቸጋሪ እና አደገኛ ሊሆንም ይችላል።
















