ኢሬቻ ፡ የ2013 ኢሬቻ በዓል አከባበር በምስል
ዓመታዊው የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ይገኛል። በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት ከዚህ በፊት እንደነበረው በርካታ ሕዝብ በበዓሉ ላይ እንደማይታደም ቀደም ሲል ተገልጾ እንደነበር ይታወሳል። በዓሉ ነገ እሁድ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማም ቀጥሎ ይከበራል። ከበዓሉ ቀደም ብሎ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ የቆየ ሲሆን የጸጥታው ጥበቃም ጥብቅ እንደሆነ ተነግሯል።












