ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች

Unai Emery

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

አርሰናል ክለቡን ለ18 ወራት ያሰለጠኑት ስፔናዊው ኡናይ ኤምሪን ከስራቸው አሰናብቷል።

ፓሪሴንት-ጀርሜይን ጋር የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ እና ከሲቪያ ጋር ሶስት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ማንሳት የቻሉት ኡናይ ኤምሪ በአርሰናል አመርቂ ውጤት ማምጣት ባለመቻላቸው ዛሬ የክለቡ አስተዳደር እንዳሰናበታቸው ገልጿል።

ክለቡ ቋሚ አሰልጣኝ እስኪያገኝ ድረስ፤ በረዳት አሰልጣኝ እና በቀድሞ የአርሰናል አማካይ ፍሬዲ ሉንበርግ በግዜያዊነት ይሰለጥናል ተብሏል።

መድፈኞቹ ባለፉት 7 ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችሉ የቀሩ ሲሆን፤ ትናንት ምሽት የዩሮፓ ሊግ የምድብ ጨዋታ በሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ፊትና በሜዳቸው በጀርመኑ ክለብ ኢንትራ ፍራክፈርት 2 ለ 1 ተሸንፈዋል።

ለመሆኑ ተሰናባቹኡናይ ኤምሪን ማን ሊተካቸው ይችላል?

ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ

የፎቶው ባለመብት, Sam Bagnall - AMA

የምስሉ መግለጫ, ኑኖ ኤስፒሪቱ ሳንቶስ

1. ኑኖ ኤስፒሪ ሳንቶስ

ኡናይን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱ አሠልጣኖች መካከል በዋነኛነት ስማቸው እየተነሳ ያለው የወቅቱ የዎልቨርሃምፕተን አሠልጣኝ ኑኖ ኤስፔሪቶ ሳንቶስ ናቸው።

ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ዎልቭስን ይዘው በፕሪሚየር ሊጉ ሰንተረዥ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ።

ማክሲሚሎኢያኖ አሌግሪኒ

የፎቶው ባለመብት, Nicolò Campo

የምስሉ መግለጫ, ማክሲሚሎኢያኖ አሌግሪኒ

2. ማሲሚ አሌግሪ

ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ኡናይ ኤምሪ ከአርሰናል ከተለያዩ በኋላ በማሲሚላኖ አሌግሪ እና በአርሰናል ክለብ መካከል ግንኙነቶች ተጀምሯል።

በቅርቡ ከጁቬንቱስ የተለያዩት አሌግሪ ከአሮጊቷ ጋር ውጤታማ የሚባል ጊዜን አሳልፈዋል።

አሌግሪ ከጁቬንቱስ ጋር አምስት የሴሪያአ እና አራት ኮፓ ኢታሊያ ዋንጫዎችን ከማንሳታቸውም በተጨማሪ ሁለት ጊዜ ለቻምፒያንስ ሊግ ፍጻሜ መድረስ ችለዋል።

ካርሎ አንቾሎቲ

የፎቶው ባለመብት, Robbie Jay Barratt - AMA

የምስሉ መግለጫ, ካርሎ አንቾሎቲ

3. አንቾሎቲ

ናፖሊን እያሰለጠኑ የሚገኙት ካርሎ አንቾሎቲ ሌላው ኡናይ ኤምረን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱት አሰልጣኞች መካከል ይገኙበታል።

ጣሊያናዊው አንቾሎቲ የውድድሩ ዘመን እስኪናቀቅ ድረስ ከናፖሊ ጋር ኮንትራት ቢኖርባቸውም፤ አሰልጣኙ ወደ ኤምሬትስ ሊያቀኑ እንደሚችል በስፋት እየተዘገበ ነው።

ብሬንዳን ሮጀርስ

የፎቶው ባለመብት, Bryn Lennon

የምስሉ መግለጫ, ብሬንዳን ሮጀርስ

4. ብሬንዳ ሮጀርስ

ሌስተር ሲቲዎች ዘንድሮ ደንቅ የሚባል የውድድር ዘመን እያሳለፉ ይገኛሉ። በብሬንዳን ሮጀርስ የሚመሩት ቀበሮዎቹ ካለፉት 10 ጨዋታዎች አርሰናልን ጨምሮ በድንቅ ጨዋታ 9 ግጥሚያዎችን በድል ማጠናቀቅ ችለዋል።

ብሬንዳን ሮጀርስ ወደ ኢሚሬትስ እንዲያቀኑ የበርካታ የአርሰናል ደጋፊዎች ምኞት ነው።

ማይክል አርቴታ

የፎቶው ባለመብት, OLI SCARFF

የምስሉ መግለጫ, ማይክል አርቴታ

5. ማይክል አርቴታ

ኡናይ ኤምሪ አርሰናልን እንዲያሰለጥኑ ከመሾማቸው በፊት፤ ክለቡን ለማሰልጠን ስሙ በስፋት ሲነሳ የነበረው ማይክል አርቴታ ነበር።

የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ባለፉት ሶስት ዓመታት ከከማንችሰተር ሲቲው ፔፕ ጋርዲዎላ ሥር ሆኖ የአሰልጠኝነትን ክህሎት ሲማር ቆይቷል።

ረዳት አሰልጣኙ አርቴታ፤ ማንችሰተር ሲቲ ሁለት የፕሪሚር ሊግ ዋንጫ፣ ሁለት የሊግ ዋንጫዎችን እና ኤፍ ኤ ዋንጫዎች እንዲያነሳ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ፓትሪክ ቪዬራ

የፎቶው ባለመብት, Rich Sellers/Offside

የምስሉ መግለጫ, ፓትሪክ ቪዬራ

6. ፓትሪክ ቪዬራ

ሌላው የቀድሞ የአርሰናል ባለታሪክ አማካይ ፓትሪክ ቪዬራ ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል እየተጠቀሰ ነው።

ቪዬራ የማይረሳውን የአርሰናል ወርቃማ የ2003/4 የድል የውድድር ዘመን አንበል በመሆን ክለቡን መርቷል።

የፈረንሳዩን ኒስ እግር ኳስ ክለብ እያሰለጠነ የሚገኘው ቪዬራ የሚፈለገውን ውጤት እያስመዘገበ ባይሆንም፤ መድፈኞቹ የቼልሲን አርዓያ የሚከተሉ ከሆነ፤ ቪዬራ የአርሰናል አሰልጣኝ ሆኖ ሊሾም እንደሚችል እየተጠቆመ ነው።

ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ

የፎቶው ባለመብት, IAN KINGTON

የምስሉ መግለጫ, ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ

7. ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ

በቅርቡ ከፖተንሃም አሰልጣኝነት የተነሱት ፖቸቲኖ፤ ሌላው ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ይሆናሉ ተብለው ከተገመቱ አሰልጣኖች መካከል ይገኙበታል።

የቶተነሃም ባላንጣ የሆነው አርሰናልን ለማሰልጠን ፍላጎት ይኖራቸው ይሆን? ሲሉ የሚጠይቁም አልጠፉም።

ፖቸቲኖ ከአርሰናል ውጪ፤ የባየር ሚዩኒክ፣ ሪያል ማድሪድ ወይም ባርሴሎና አሰልጣኝ ለሆኑ እንደሚችሉ በስፋት እየተገመተ ይገኛል።