የቀድሞ የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የሞቱት "በካንሰር" ነው ተባለ

ሮበርት ሙጋቤ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የቀድሞ የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ለካንሰር ህክምና ይደረግላቸው የነበረው የኬሞቴራፒ ህክምና ሲቋረጥ እንደሞቱ የአገሪቱን ፕሬዝዳንት ኤመርሰንን ምናንጋግዋንን ጠቅሶ የአገሪቱ ሄራልድ ጋዜጣ ዘግቧል።

ሙጋቤ ይታከሙበት የነበረው የሴንጋፖሩ ሆስፒታል ዶክተሮች የሙጋቤ ኬሞቴራፒ እንዲቋረጥ ያደረጉት በሁለት ምክንያቶች እንደሆነ ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ገልፀዋል።

እሳቸው እንዳሉት ሮበርት ሙጋቤ እንድሜአቸው የገፋ በመሆኑና ካንሰሩም በሰውነታቸው ተስፋፍቶ ስለነበር ኬሞቴራፒው ብዙ ጠቀሜታ ስላልነበረው እንዲቆም ተወስኗል።

ዚምባብዌን ከነፃነት ጀምሮ ለ37 ዓመታት የመሩት የ95 ዓመቱ ሮበርት ሙጋቤ በመፈንቅለ መንግሥት ከስልጣን የተወገዱት እአአ በ2017 ነበር።

ለወራት ተኝተው ይታከሙ በነበረበት የሴንጋፖር ሆስፒታል ህይወታቸው ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነበር።

ከዚምባብዌ መዲና ሃራሬ ወጣ ብሎ በሚገኝና በግንባታ ላይ በሚገኝ የነፃነት ታጋዮች የመቃብር ስፍራ እንደሚቀበሩም ተገልጿል።