የሊዮ ቶልስቶይ መፅሐፍ ህንዳውያን 'አክቲቪስቶች' ላይ መዘዝ አምጥቷል
![የሊዮ ቶልስቶይ [War and Peace] መፅሐፍ](https://ichef.bbci.co.uk/ace/ws/640/cpsprodpb/1499/production/_108537250_719c5107-7645-47a2-801c-88970884bc70.jpg.webp)
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የሊዮ ቶልስቶይ [War and Peace] መፅሐፍ ከሰሞኑ ሕንድ ውስጥ መነጋገሪያ ሆኗል። ምክንያቱ ደግሞ ሕንዳውያኑ 'አክቲስቶች' መፅሐፉን ለምን ያዛችሁ ተብለው መጠየቃቸው ነው።
ቬርነኖን ጎንሳልቬስ የተባለው ሕንዳዊ ተሟጋች ሰኞ ዕለት ክሱን ሊከታተል ፍርድ ቤት ሲቀርብ ከተጠየቀው ጥያቄ መካከል አንዱ 'ለምን ይህንን መፅሐፍ ይዘህ ተገኘህ?' የሚል ነበር።
ቬርኖን እና ሌሎች አራት ጓደኞቹ አመፅ ቀስቅሳችኋል ተብለው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት በያዝነው ወር ነው።
የዳኛው ጥያቄ ሕንዳውያን ወደ ማሕበራዊ ድር-አምባ ዘምተው በጉዳዩ ላይ እንዲመክሩ እና እንዲሳለቁ አድርጓቸዋል።
ፖሊስ የአምስቱን ሰዎች ቤት ሲበረብር በርካታ መፃሕፍት፣ ሲዲዎች እና ሌሎች አነሳሱት ከተባለው አመፅ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ንብረቶች ያገኛል።
ከእነዚህ መካከል አንዱ የሌዎ ቶልስቶይ መፅሐፋ [War and Peace] ነው። ይህን የተረዱት ዳኛ 'ለምን ይሆን ይህንን መፅሐፍ ቤትህ ሊገኝ የቻለው? እስቲ ለፍርድ ቤቱ አስረዳ' ብለው ይጠይቁታል።
አልፎም 'የመንግሥትን ጭቆና መቃወም' የሚል ርዕስ የተሰጠው ሲዲ መገኘቱ ሞጋቾቹ ከአገዛዙ ጋር አንድ የሆነ ቅራኔ እንዳላቸው የሚያሳይ ነው ሲሉ ዳኛው ተናግረዋል።
ፖሊስ አምስቱ ሰዎች ባነሳሱት የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያት ብዙ ጥፋት ደርሷል፤ የአንድ ሰው ሕይወትም ጠፍቷል ሲል ግለሰቦቹን ይከሳል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
በርካታ ሕንዳውያን ግን የሰዎቹ መታሠርም ሆነ መሰል ጥያቄ መጠየው 'የመናገር ነፃነትን' የሚጋፋ ነው ሲሉ ይቃወሙታል።
የዳኛው ጥያቄ ያስደነቃቸው ብዙዎች ወደ ትዊተር አምባ በመዝለቅ በሁኔታው ምን ያህል እንደተደነቁና እንደተበሳጩ እየገለፁ ነው። አልፎም በርካቶች መደርደሪያቸው ላይ ያሉ መፃሕፍትን ፎቶ በማንሳትና በማጋራት ክስተቱን እየተቃወሙት ይገኛሉ።













