BBC News,
አማርኛ
ወደ ዋናው ይዘት ይለፉ
ክፍሎች
ዜና
ኢትዮጵያ
ፖለቲካ
ሴቶች
ጤና
ስፖርት
ጥበብ
ቴክኖሎጂ
ምጣኔ ሃብት
ቪዲዮ
በጣም የተወደዱ
ዜና
ኢትዮጵያ
ፖለቲካ
ሴቶች
ጤና
ስፖርት
ጥበብ
ቴክኖሎጂ
ምጣኔ ሃብት
ቪዲዮ
በጣም የተወደዱ
የቡራዩ ተፈናቃዮች በምስል
ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ
17 መስከረም 2018
በሳምንቱ የመገባደጃ ቀናት ቡራዩ ከተማ በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲጠፋ፥ በርካታ ቁጥር ያላቸው ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሸሽተዋል።
የምስሉ መግለጫ,
ብሔር ላይ ያነጣጠሩ ናቸው በተባሉት አሸዋ ሜዳ፣ ከታ፣ ቡራዩ አካባቢዎች በተፈፀሙት ጥቃቶች የንብረት መውደም እና ዝርፊያ መፈፀሙ ታውቋል።
የምስሉ መግለጫ,
ይህንን ጥቃት ተከትሎ ዛሬ በአዲስ አበባ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል.
የምስሉ መግለጫ,
ከተፈናቃዮቹ መካከል አንዱ የሆነ ወጣት በወረዳ 11 ወጣት ማዕከል
የምስሉ መግለጫ,
ተፈናቃዮቹ ቀድመው ከነበሩበት ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፊሊጶስ ትምህርት ቤት ወጥተው ነው ወደ ወረዳ 11 ያመሩት
የምስሉ መግለጫ,
ተፈናቃዮቹ ወረዳ 11 ወጣት ማዕከል ቅጥር ግቢ ተጠልለው እንዳሉ ዘጋቢያችን መታዘብ ችሏል።
የምስሉ መግለጫ,
ከተፈናቃዮቹ መካከል መካከል የሆነች አንዲት እናት ልጇን እንዳዘለች በወረዳ 11 ወጣት ማዕከል ውስጥ ተጠልላለች።
የምስሉ መግለጫ,
በጥቃቱ 23 ሰዎች ሲሞቱ በጥቃቱ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 200 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልፀዋል።
የምስሉ መግለጫ,
በርካታ ሕፃናት፣ ታዳጊዎችና እና እናቶች ከተፈናቃዮቹ መካከል ይገኙበታል።
የምስሉ መግለጫ,
ከቅዳሜ ምሽት አንስቶ በአስኮ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ተጠልለው የቆዩ ተፈናቃዮች በአምስት አውቶብሶች በቅርብ ወደሚገኝ ትምህርት ቤት ተወስደዋል.
You might also like:
news
|
sport
|
weather
|
worklife
|
travel
|
future
|
culture
|
world
|
business
|
technology