በአዲስ አበባ ከተማ ሊታዩ የሚገባቸው 5 ታሪካዊ ቤቶች

የአፈንጉስ አጥናፍ ሰገድ ቤት ካዛንችስ አከባቢ የሚገኘ ሲሆን አሁን የልቤ ፋና ት/ቤት ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል። ይህ ቤት የተገነባው በ1884 ዓ.ም ሲሆን የቤቱ ባለቤት የነበሩት አፈንጉስ አጥናፍ ሰገድ ከፋሽስት ጣሊያን ጦር ጋር በተደርጋው የማይጨው ጦርነት ላይ ተሰውተዋል።