በዓለም እና በአፍሪካ የመጀመሪያ የተባሉ የኦሊምፒክ ታሪኮችን ያስመዘገበው ኢትዮጵያዊ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የክብር ዘብ አባል የነበረው አበበ ቢቂላ በኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር ታሪክ ውስጥ ለዘላለም ስሙ በክብር ሲነሳ የሚኖርበትን ታሪክ ሠርቷል።

አበበ በአትሌቲክስ ውድድር ውስጥ ዋነኛው እና ፈታኝ በሆነው የማራቶን ውድድር ጣልያን ሮም ላይ 42 ኪሎ ሜትር ርቀትን በባዶ እግሩ በመሮጥ አሸናፊ ሲሆን ዓለምን ከማስደነቁ ባሻገር በታላቁ የኦሊምፒክ ውድድር ላይ የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ለመሆን ችሏል።

ከዚያም በኋላ ሮምን ተከትሎ ጃፓን ቶኪዮ ላይ በተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር በድጋሚ በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሲሆን ደግሞ በተከታታይ የውድድሩ አሸናፊ በመሆን በዓለም ላይ ቀዳሚው አትሌት ለመሆን በቅቷል።

ይህ የአበበ ቢቂላ ድል ኢትዮጵያውያን ብሎም አፍሪካውያን በዓለም የአትሌቲክስ መድረክ ላይ አሁን ድረስ የበላይ እንዲሆኑ በር የከፈተ ነው።