ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ የተፈጸመበት ቅጽበት

ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ የተፈጸመበት ቅጽበት

ይህ ቪዲዮ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ የተፈጸመበትን ቅጽበት ያሳያል።

ትራምፕ በፔንስልቪንያ ግዛት ለደጋፊዎቻቸው ንግግር እያደረጉ ሳለ በርካታ የተኩስ ድምጾች ተሰምተዋል።

የመንግሥት የደኅንነት ሠራተኞች (ሴክሬት ሰርቪስ አባላት) የቀድሞ ፕሬዝዳንቱን ለመከላከል በፍጥነት ወደ መድረክ በመውጣት ዝቅ አድርገዋቸው ከሚተኮሰው ጥይት ሲከላከሉ ታይተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ዝቅ ካሉበት ሲነሱ ፊታቸው እና ቀኝ ጆሯቸው ደም የታየበት ሲሆን፤ የግድያ ሙከራው ከተፈጸመባቸው ስፍራ ወደተዘጋጀላቸው መኪና ሲወሰዱ ቀኝ እጅቸውን በማንሳት የአይበገሬነት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በምላሹም ደጋፊዎቻቸውም “ዩ ኤስ ኤ! ዩ ኤስ ኤ! ዩ ኤስ ኤ!” ሲሉ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።