ዩክሬን በሩሲያ ላይ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ እያካሄደች እንደሆነ ተገለጸ

መድፍ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ሳምንቱ የዩክሬን መልሶ ማጥቃት ዘመቻ የታየበት እንደሆነ ተገልጿል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን “የዩክሬን መልሶ ማጥቃት ዘመቻ ተጀምሯል” ብለዋል።

በእርግጥ ለተወሰኑ ሳምንታት የመልሶ ማጥቃት ዘመቻው እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል።

ዩክሬን “ኦፕሬሽኖችን መቀየስ” የሚል መጠሪያ ነው የሰጠችው።

የረዥም ርቀት መሣሪያ እና ሚሳኤል መጠቀሟ ተገልጿል።

ወደ ሩሲያ ድንበር አቅራቢያ የዩክሬን ወታደሮች ታጥቀው መጓዛቸው ተገልጿል።

የዩክሬን ደኅንነትና ትብብር ማእከል አጋር መሥራች ሼሪ ኩዛን የሩሲያን መከላከያ ላይ ዘመቻ የሚከፈትበት ሂደት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የተወሰኑ ተንቀሳቃሽ ምሥሎችና አስተያየቶች እንደሚጠቁሙት የዩክሬን ኃይል መሰናክል አላጣውም።

“አንዳንድ አካባቢዎች ድል አለ። አንዳንድ አካባቢዎች አነስተኛ ሽንፈት አይጠፋም” ሲሉ አጋር መሥራቹ ተናግረዋል።

ከዛፖሪዛዚሃ በስተ ደቡብ በሚገኙ አካባቢዎች ውጊያ እንዳለ ከመግለጽ በዘለለ በየትኞቹ ቦታዎች ምን እንደተከሰተ በዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ባለፈው ሳምንት በዲኒፖ ወንድ የተገነባው ግድብ ከሩሲያ በተሰነዘረ ጥቃት ፈርሷል የሚለው ከተገለጸ በኋላ የበርካቶች ትኩረት በጎርፍ የተጎዱ ሰዎች ጉዳይ ሆኗል።

የዩክሬን ወታደሮች ከዚህ ቀደም በዚህ መንገድ ወደ ኼርሶን መግባታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ግድቡ ላይ ሩሲያ ጥቃት የሰነዘረችው የዩክሬን ወታደሮችን ጉዞ ለማስቆም መሆኑም ተገልጿል።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ የዩናይትድ ኪንግደም የመከላከከያ ሚኒስትር “በተለያዩ ግንባሮች ከፍተኛ ውጊያ ቀጥሏል። ዩክሬን ናት መነሻውን የያዘችው” ሲሉ ትዊት አድርገዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾይጉ የሩሲያ ኃይሎች የዩክሬን ወታደሮችን ጥቃት እንደመከቱ ገልጸዋል።

ወታደሮቹ 1,500 እንደሚደርሱም ተገልጿል።

የዩክሬን 47ኛ ሜካናይዝድ ብርጌድ የሩሲያ መስመር አልፎ ለመግባት መሞከሩ ተገልጿል።

የዩክሬን አመራሮች አሁን እየተካሄደ ስላለው ኦፕሬሽን ብዙም መረጃ እየሰጡ አይደለም።

የአገሪቱ ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ሀና ማሊር “የመከላከል ሥራ ሠርተዋል” ከማለት የዘለለ ምንም አላሉም።

በዩክሬን እና በሩሲያ መስመሮች መካከል ውጊያው ሲቀጥል፣ ዩክሬን ወደ ሩሲያ ዘልቃ ለመግባት እንደምትሞክር ተንታኞች ገልጸዋል።

ሩሲያን የሚደግፉ የቴሌግራም ቡድኖች የዩክሬን ኃይል የሩሲያ ወታደሮች “የሚጠብቁት ቦታ መግባቱ” በስላቅ ተገልጿል።

ዩክሬን ዘልቆ ለመግባት ብዙ ወታደሮች እንደምታጣና ያሏት ወታደሮች በቂ ይሆኑ እንደሆነም የጠየቁ አሉ።

ከባኽሙት በስተደቡብ እና በሌሎች አካባቢዎችም ዩክሬን መልሶ ማጥቃት እያካሄደች መሆኑ ሲነገር ቆይቷል።

የአገሪቱ ብሔራዊ ደኅንነትና መከላከያ ምክር ቤት ጸሐፊ ኦልኪሲ ዳኒሎቭ ግን ይህ እውነት እንዳልሆነ ገልጸዋል።

“መልሶ ማጥቃት ዘመቻውን ስናካሂድ ሁላችሁም ታውቁታላችሁ። ታዩታላችሁ” ብለዋል።

ዩክሬን ለእግረኛ ወታደሮቿ ድጋፍ የሚሰጥ ተዋጊ ጀት እጥረት ስላለባት እንደ አንድ መሰናክል ይወሰዳል።

ሌላው ውስንነት የጊዜ ጉዳይ ነው። ከአምስት ወራት በላይ የሚወስድ ኦፕሬሽን ሲሆን ወደ ዝናባማ ወቅት እየገባች መሆኑ ደግሞ መሣሪያ ለማንቀሳቀስ አስቸጋሪ ያደርገዋል።

ዩክሬን ወደ ሩሲያ ዘልቃ መግባት ከቻለችና ሩሲያን ከክሬሚያ ጋር የሚያገናኘውን ኬርች ድልድይ መስበር ከቻለች ትልቅ ድል እንደሚሆንን ይህ ግን ከሆነም ከወራት በኋላ እንደሚሆን ተጠቁሟል።