የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወሳኝ ሳምንት ጨዋታዎች የውጤት ግምቶች

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ መጠናቀቂያው ተቃርቧል።
የሊጉ 36ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ ተጀምረው እሑድ እና ሰኞ ቀጥለው ይከናወናሉ።
ለሊጉ ዋንጫ እና ላለመውረድ ከሚደረገው ትንቅንቅ በተጨማሪ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ የሚደረገው ፉክክርም አጓጊ ሆኗል።
የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን በየሳምንቱ እንደሚያደርገው የዚህን ሳምንት ጨዋታዎች ውጤት እንደሚከተለው ገምቷል።
ቅዳሜ

ሊድስ ከ ኒውካስል
ሊድሶች ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ሲቲ ቢሸነፉም በማብቂያ ደቂቃዎች ላይ ባሳዩት አቋም የልብ ልብ የሚሰማቸው ይመስለኛል።
ይህን ጨዋታ ቢያሸንፉ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ቢረዳቸውም የሚያሳኩት አይመስለኝም።
ባለፈው ሳምንት የተሸነፉት ኒውካስሎች እስከ አራተኛ ደረጃ ያለውን ቦታ ይዘው ለማጠናቀቅ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።
ሊድስ በሳም አላርዲየስ የመልሶ ማጥቃት ሊጫወት ቢሞክርም የኒውካስል አጥቂዎችን ግን የሚቋቋም የተከላካይ ክፍል የለውም።
ውጤት፡ 1 – 3
አስቶን ቪላ ከ ቶተንሃም
ይህን ጨዋታ ቪላ ከሁለት የጎል ልዩነት በላይ ካሸነፍ በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ከቶተንሃም በላይ ይቀመጣል።
ጨዋታው አቻ ይጠናቀቃል ብሎ መገመት ጥሩ አማራጭ ነው።
ቪላ በቅርቡ ሁለት ጊዜ ነጥብ ቢጥልም የቶተንሃም አቋም መለዋወጥ ለመገመት ከባድ ሆኗል።
የኡናይ ኤምሬ ቡድን የመጀመሪያውን ጨዋታ 2 ለምንም በማሸነፉ ይህንንም ጨዋታ ያሸንፋል ብዬ እገምታለሁ።
ውጤት፡ 2 – 1

ቼልሲ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት
ለዚህ ጨዋታ ኖቲንግሃም ፎረስትን ከሜዳ ውጭ ያለውን ደካማ ውጤት ከግምት አስገባለሁ።
ፎረስቶች ከሜዳቸው ውጭ ካደረጓቸው ስድስት ጨዋታዎች አንዱን አሸንፈው በአማካይ 2.4 ጎሎችን አስተናግደዋል።
ቼልሲዎች ባለፈው ሳምንት ማሸነፍ ባይኖርባቸውም ሦስቱን ነጥብ አሳክተዋል።
አሁን ደግሞ ፍራንክ ላምፓርድ በሜዳው ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።
ውጤት፡ 2 – 1
ክሪስታል ፓላስ ከ በርንመዝ
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ፓላስ በርንመዝን አሸንፎ ነበር።
የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞችን ቡድናቸውን ጥሩ አድርገዋል።
ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል።
ውጤት፡ 1 – 1

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ዎልቭስ
የማንቸስተር ዩናይትድ ጉዳይ ኣሳቢ ነው። ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ከመሸነፋቸውም በላይ በ315 ደቂቃዎች አንድ ጎል ብቻ አስቆጥረዋል።
ከሜዳቸው ውጭ እየተቸገሩ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ለመያዝ ከሊቨርፑል ጋር እየተፎካከሩ ነው።
በዩለይን ሎፕቴጊዩ ስር የተዳረጁ የሚመስሉት ዎልቭሶች ከሁለት ሳምንት በፊት በብራይተን ከፍተኛ ሽንፈት አስተናግደዋል።
ዴቪድ ደ ጊያ ስህተት እስካልሠራ ድረስ የኤሪክ ቴን ሃግ ቡድን ጨዋታውን ያሸንፋል።
ውጤት፡ 2 – 0
ሳውዝሃምፕተን ከ ፉልሃም
ከበርንመዝ ጨዋታ በኋላ ሳውዝሃምፕተን ያሸንፋል ብዬ ስለማልገምት ይህን ጨዋታ ፉልሃም ያሸንፋል።
ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ጥሩ ቢፎካከሩም ከሽንፈት አልዳኑም።
በሂሳባዊ ስሌት ከሊጉ ባይወርዱም ሁሉም እንደሚያውቀው ወርደዋል ማለት ይቀላል።
አሌክሳንደር ሚትሮቪች በቅጣት ባይሰለፍም ፉልሃም አሁንም በማራኪ እና በማጥቃት ላይ በተመሠረተው አጨዋወታቸው ቀጥለዋል።
ውጤት፡ 1 – 2

እሑድ
ብሬንትፎርድ ከ ዌስት ሃም
ዕድል ካልጠመመባቸው በስተቀር ዌስት ሃሞች የመውረድ ዕጣቸው ያከተመ ይመስላል።
በሊጉ መቆየታቸውን ሙሉ በሙሉ ስላልተረጋገጠ ግን በዩሮፓ ኮንፈረንስ ከኤዜድ አልክማር ጋር የሚኖራቸውን የመልስ ጨዋታ ከግምት ያስገባ ሁለት ቡድን ማሰብ አለባቸው።
ይህን ከግምት በማስገባት ጨዋታው ከባድ ሊሆንባቸው ይችላል። በመጀመሪያው ጨዋታ ብረንትፎርድ ማሸነፉን እናስታውሳለን።
ውጤት፡ 2 – 0

ኤቨርተን ከ ማንቸስተር ሲቲ
ይህ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ከሪያል ማድሪድ ጋር ባለው የመልስ ፍልሚያ ይወሰናል።
ኤቨርተኖች በመልሶ ማጥቃት ብራይተንን ማሸነፍ ችለዋል።
በዚህ ጨዋታም ተመሳሳይ አጨዋወት ቢከተሉም የመጀመሪያዋ ጎል ውጤቱን ትወስናለች።
ኤቨርተኖች በሲቲ ቢሸነፉም ከቀሪ ጨዋታቸው አንዱን አሸንፈው በሊጉ የመቆየት ዕድል አላቸው።
ለአሁኑ ሌስተር እና ሊድስ ሳውዝሃምፕተንን ተከትለው ሊወርዱ እንደሚችሉ እገምታለሁ።
ውጤት፡ 1 – 2

አርሰናል ከ ብራይተን
ሁለቱም ቡድኖች ለዚህ ጨዋታ ያላቸውን አቀራረብ ማየት እፈልጋለሁ።
ብራይተኖች እንደኤቨርተን ከሚከላከል ቡድን የሚያጠቃቸውን ቡድን ይመርጣሉ።
5 ለ 1 የደረሰባቸው ሽንፈት የአጨዋወት ዘይቤያቸውን አይቀይረውም።
ማይክል አርቴታም በዚህ ጨዋታ በማጥቃት ላይ ተመስርተው ይጫወታሉ።
ጨዋታው ክፍት ከመሆኑ ባለፈ በርካታ ጎሎችን አስተናግዶ በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል።
ውጤት፡ 2 – 2

ሰኞ

ሌስተር ከ ሊቨርፑል
ጀምስ ማዲሰን በፉልሃም ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ የቡድን አጋሮቹን መተቸቱ ተገቢ ቢሆንም እሱም ከዚህ ትችት አያመልጥም።
ሌስተሮች ውጤታማ ቢሆኑባቸውም ያለፉትን ስደስት ጨዋታዎች አሸንፈው የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ለማግኘት ከሚጥሩት ሊቨርፑሎች ትልቅ ፈተና ይገጥማቸዋል።
ሊቨርፑሎች አሁን ጠንካራ ሲሆኑ የሌስተር ተከላካይ መስመር ደግሞ ደካማ ነው።
በማጥቃት ላይ የሚመሠረተው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አዝናኝ እንደሚሆን እገምታለሁ። ሌስተሮች ጎል ቢያስቆጥሩም ሊቨርፑሎች በርካታ ኳሶችን ከመረብ ያገናኛሉ።
ውጤት፡ 1 – 3












