ሐሰተኛ ዜናዎችን እንዴት ልንለይ እና ልንገታ እንችላለን?

ሐሰተኛ ዜና በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ አዲስ ነገር አይደለም። ነገር ግን ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት የኢንተርኔት በተለይም የማኅበራዊ ሚዲያ መስፋፋት የተሳሳተ መረጃ ስርጭትን ችግሩ አሳሳቢ አድርጎታል። እንደ መረጃ ፈላጊ እና ተጠቃሚ አንድ ሰው ሐሰተኛ ዜናን እንዴት ሊለይ እና እንዳይስፋፉ ሊያደርግ ይችላል?