የተወዳጁ የካርቱን ፊልም ገጸ ባህሪ የ'ሚኪ ማውስ' ድምጽ እንዴት አሁን ያለበትን ሊመስል ቻለ?
የሚኪ ማውስን የተባለው የካርቱን ፊልም ገጸ ባህሪ በመላው ዓለም ከሕጻናት አልፎ በአዋቂዎች ይወደዳል። አንድ መቶ ዓመት ሊሆነው የተቃረበውን ይህንን ገጸ ባህሪይ በድምጽ ወክለው እስካሁን የተጫወቱት አራት ሰዎች ብቻ ናቸው።
የሚኪ ማውስ ፈጣሪ የሆነው የግዙፉ የዋልት ዲዝኒ የፊልም ኩባንያ ባለቤት እራሱ ነበር ከ1929 እስከ 1946 ድረስ የሚኪ ማውስን ድምጽ ወክሎ የሠራዉ፤ ግን ብዙ ሰው አያውቀውም።
በዚህም ምክንያት የዋልት ዲዝኒ የመጀመሪያ ድምጽ አሁን ድረስ የካርቱን ፊልም ገጸ ባህሪዩን ወክለው በሚጫወቱት ላይ ተጽዕኖውን አሳድሮባቸዋል።









