እንዴት አንድ አንበጣ ወረርሽኝ እንደሚሆን
ከወራት በፊት ግዙፍ የበረሃ አንበጣ መንጋ የአፍሪካ ቀንድንና ደቡብ እስያን እያካለለ ያገኘውን ሰብል በማውደም የአካባቢውን ሕዝብ የምግብ አቅርቦትና ህይወት አደጋ ላይጥሎ ነበር። አሁንም በድጋሚ በድጋሚ እየተራባ ይገኛል። ይህም በ25 ዓመት ውስጥ ያጋጠመ የከፋ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ነው። እንዴት እዚህ አስከፊ ደረጃ ላይ ደረሰ?

የይህን የሚመስለው የበረሃ አንበጣ ተነጥሎ ብቻውን የሚኖር ነው። ከእንቁላል ተነስቶ በማደግ መብረር የሚችል አንበጣ ይሆናል። ቀላልና ብዙም ያልጎላ አኗኗር አለው።

አንድ አንበጣ በተከታታይ በተለያዩ ደረጃዎች ውስጥ ያልፋል። ቁጥራቸው በሚያንስበትና የሚበሉት ሰብል በሚያጥርበት ጊዜ በብቸኝነት መኖራቸውን በመተው በጋራ ይሆናሉ።
በዚህ ወቅት ቀለማቸውን በመቀየር በቡድን የሚጓዝ አውዳሚ መንጋን ይፈጥራሉ።
እንዲህ ያለው የአንበጣ መንጋ ግዙፍ ሊሆን ይችላል። ቁጥራቸውም እስከ 10 ቢሊየን፤ የሚሸፍኑትም ቦታ በመቶዎች ኪሎ ሜትር ሊሆን ይችላል። የአንበጣ መንጋው በቀን እስከ 200 ኪ.ሜ በመሸፈን ያገኙትን እየበሉ በመራባት የአርሶ አደሮችን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላሉ።
ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና የእርሻ ድርጅት እንዳለው አማካይ የአንበጣ መንጋ 2500 ሰዎችን ለዓመት የሚመግብ ምርትን ሊያወድም ይችላል።
ከ15 ዓመት በፊት በምዕራብ አፍሪካ ተከስቶ የነበረ የአንበጣ መንጋ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የሰብል ውድመትን ማስከተሉን የተባበሩት መንግሥታት ገልጿል።
ከ60 ዓመታት በፊትም ከባድ የሚባሉ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ አጋጥሞ ነበር። ክስተቶቹም በርካታ አህጉራትን ያካተቱ ስለነበሩ "ወረርሽኝ" ከሚባሉበት ደረጃ ላይ ደርሰው ነበር።
የመንግሥታቱ ድርጅት እንደሚገምተው የበረሃ አንበጣ ከምድራችን 10 ነዋሪዎች የአንዱን ህይወት ይነካል። ይህም አንበጣን ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀስ አደገኛ ፍጥረት አስብሎታል።
የይህን የሚመስለው የበረሃ አንበጣ ተነጥሎ ብቻውን የሚኖር ነው። ከእንቁላል ተነስቶ በማደግ መብረር የሚችል አንበጣ ይሆናል። ቀላልና ብዙም ያልጎላ አኗኗር አለው።
አንድ አንበጣ በተከታታይ በተለያዩ ደረጃዎች ውስጥ ያልፋል። ቁጥራቸው በሚያንስበትና የሚበሉት ሰብል በሚያጥርበት ጊዜ በብቸኝነት መኖራቸውን በመተው በጋራ ይሆናሉ።
በዚህ ወቅት ቀለማቸውን በመቀየር በቡድን የሚጓዝ አውዳሚ መንጋን ይፈጥራሉ።
እንዲህ ያለው የአንበጣ መንጋ ግዙፍ ሊሆን ይችላል። ቁጥራቸውም እስከ 10 ቢሊየን፤ የሚሸፍኑትም ቦታ በመቶዎች ኪሎ ሜትር ሊሆን ይችላል። የአንበጣ መንጋው በቀን እስከ 200 ኪ.ሜ በመሸፈን ያገኙትን እየበሉ በመራባት የአርሶ አደሮችን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላሉ።
ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና የእርሻ ድርጅት እንዳለው አማካይ የአንበጣ መንጋ 2500 ሰዎችን ለዓመት የሚመግብ ምርትን ሊያወድም ይችላል።
ከ15 ዓመት በፊት በምዕራብ አፍሪካ ተከስቶ የነበረ የአንበጣ መንጋ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የሰብል ውድመትን ማስከተሉን የተባበሩት መንግሥታት ገልጿል።
ከ60 ዓመታት በፊትም ከባድ የሚባሉ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ አጋጥሞ ነበር። ክስተቶቹም በርካታ አህጉራትን ያካተቱ ስለነበሩ "ወረርሽኝ" ከሚባሉበት ደረጃ ላይ ደርሰው ነበር።
የመንግሥታቱ ድርጅት እንደሚገምተው የበረሃ አንበጣ ከምድራችን 10 ነዋሪዎች የአንዱን ህይወት ይነካል። ይህም አንበጣን ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀስ አደገኛ ፍጥረት አስብሎታል።
| ዓመት | ዝቅተኛ ቁጥር | ማሻቀብ ወይም መቀነስ | ወረርሽኝ |
| 2019 | 0 | 18 | 0 |
| 2018 | 0 | 0 | 0 |
| 2017 | 0 | 0 | 0 |
| 2016 | 5 | 0 | 0 |
| 2015 | 2 | 0 | 0 |
| 2014 | 7 | 0 | 0 |
| 2013 | 10 | 0 | 0 |
| 2012 | 9 | 0 | 0 |
| 2011 | 7 | 0 | 0 |
| 2010 | 4 | 0 | 0 |
| 2009 | 5 | 0 | 0 |
| 2008 | 8 | 0 | 0 |
| 2007 | 13 | 0 | 0 |
| 2006 | 1 | 0 | 0 |
| 2005 | 0 | 20 | 0 |
| 2004 | 0 | 23 | 0 |
| 2003 | 5 | 0 | 0 |
| 2002 | 0 | 0 | 0 |
| 2001 | 0 | 0 | 0 |
| 2000 | 2 | 0 | 0 |
| 1999 | 4 | 0 | 0 |
| 1998 | 7 | 0 | 0 |
| 1997 | 12 | 0 | 0 |
| 1996 | 15 | 0 | 0 |
| 1995 | 15 | 0 | 0 |
| 1994 | 13 | 0 | 0 |
| 1993 | 20 | 0 | 0 |
| 1992 | 5 | 0 | 0 |
| 1991 | 0 | 0 | 0 |
| 1990 | 3 | 0 | 0 |
| 1989 | 0 | 15 | 0 |
| 1988 | 0 | 0 | 26 |
| 1987 | 15 | 0 | 0 |
| 1986 | 12 | 0 | 0 |
| 1985 | 2 | 0 | 0 |
| 1984 | 0 | 0 | 0 |
| 1983 | 7 | 0 | 0 |
| 1982 | 5 | 0 | 0 |
| 1981 | 5 | 0 | 0 |
| 1980 | 6 | 0 | 0 |
| 1979 | 0 | 4 | 0 |
| 1978 | 0 | 15 | 0 |
| 1977 | 3 | 0 | 0 |
| 1976 | 9 | 0 | 0 |
| 1975 | 7 | 0 | 0 |
| 1974 | 11 | 0 | 0 |
| 1973 | 7 | 0 | 0 |
| 1972 | 5 | 0 | 0 |
| 1971 | 4 | 0 | 0 |
| 1970 | 7 | 0 | 0 |
| 1969 | 0 | 11 | 0 |
| 1968 | 0 | 25 | 0 |
| 1967 | 7 | 0 | 0 |
| 1966 | 2 | 0 | 0 |
| 1965 | 4 | 0 | 0 |
| 1964 | 6 | 0 | 0 |
| 1963 | 0 | 10 | 0 |
| 1962 | 0 | 29 | 0 |
| 1961 | 0 | 29 | 0 |
| 1960 | 0 | 0 | 44 |
| 1959 | 0 | 0 | 47 |
| 1958 | 0 | 0 | 41 |
| 1957 | 0 | 0 | 37 |
| 1956 | 0 | 0 | 35 |
| 1955 | 0 | 0 | 43 |
| 1954 | 0 | 0 | 40 |
| 1953 | 0 | 0 | 43 |
| 1952 | 0 | 0 | 27 |
| 1951 | 0 | 41 | 0 |
| 1950 | 0 | 33 | 0 |
| 1949 | 9 | 0 | 0 |
| 1948 | 12 | 0 | 0 |
| 1947 | 0 | 29 | 0 |
| 1946 | 0 | 36 | 0 |
| 1945 | 0 | 0 | 42 |
| 1944 | 0 | 0 | 47 |
| 1943 | 0 | 0 | 43 |
| 1942 | 0 | 0 | 35 |
| 1941 | 0 | 24 | 0 |
| 1940 | 0 | 6 | 0 |
| 1939 | 5 | 0 | 0 |
| 1938 | 3 | 0 | 0 |
| 1937 | 6 | 0 | 0 |
| 1936 | 6 | 0 | 0 |
| 1935 | 6 | 0 | 0 |
| 1934 | 0 | 9 | 0 |
| 1933 | 0 | 18 | 0 |
| 1932 | 0 | 0 | 27 |
| 1931 | 0 | 0 | 35 |
| 1930 | 0 | 0 | 45 |
| 1929 | 0 | 0 | 41 |
| 1928 | 0 | 0 | 34 |
| 1927 | 0 | 22 | 0 |
| 1926 | 0 | 8 | 0 |
| ምንጭ፡ FAO | |||
| ማስታወሻ፡ 'ዝቅተኛ ቁጥር' ማለት አንበጣዎች የሚሸፍኑት ቦታ ትንሽ ሲሆን፤ 'ማሻቀብ' ደግሞ አንበጣዎቹ እየተራቡ በርካታ ወረርሽኝ እንዲፈጠር ሲያደርጉ ነው። 'ወረርሽኝ' ማለት ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ሰፊ ቦታን የሚሸፍን የአንበጣ መንጋ ከዓመት በላይ ሲከሰት ነው። ወረርሽኙ ሲያበቃ ደግሞ 'መቀነስ' ይባላል። | |||
አዲስ የአንበጣ መንጋ እየተፈለፈለ ነው።
ከሦስት ወራት በፊት ያጋጠመው የአንበጣ መንጋ በአስር ዓመታት ውስጥ ካጋጠመው የከፋው ሲሆን፤ ጂቡቲን፣ ኢትዮጵያንና ሶማሊያን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድን በማዳረስ ሰብሎችንና የእንስሳ ግጦሽን አውድሟል። ይህም የአካባቢውን አገራት የምግብ ደህንነት አደጋ ላይ ጥሎታል።
የአንበጣ መንጋው በጥርና በየካቲት በፍጥነት ተዛምቶ ኢትዮጵያን፣ ሶማሊያንና ኬንያን በማዳረስ በምሥራቅ አፍረካ ተዛምቷል። ወረርሽኙ ለኢትዮጵያና ለሶማሊያ በ25 ዓመት እንዲሁም ለኬንያ ደግሞ በ70 ዓመት ውስጥ ካጋጠሟቸው የከፋው ነው።
የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ስጋቱን እንደገለጸው ከሆነ ከመጋቢት በኋላ ያለው እርጥብ የአየር ሁኔታ ሁለተኛ ዙር የአንበጣ አንበጣ ወረርሽኝ በማስከተል በአካባቢው ሕዝብ ህይወት ላይ "ታይቶ የማያውቅ ስጋትን" ደቅኗል።
የአንበጣ መንጋውን የመቆጣጠሩ ሥራ በፍጥነት ካልተከናወነ መንጋው በ20 እጅ ሊጨምር እንደሚችል ፋኦ አስጠንቅቋል።
በአንበጣ ስጋት ውስጥ ያሉ አገራት ቁጥር

ይህም በግጭቶች፣ በድረቅና በጎርፍ ምክንያት ከፍተኛ የምግብ እጥረት ባለበት በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ከባድ ጉዳትን ያስከትላል። በተጨማሪም የአንበጣ መንጋው እየተራባ ባለባቸው በኢራንና በየመን ጉዳቱ የባሰ እንደሚሆን ፋኦ ገልጿል።
እስካሁንም በምሥራቅ አፍሪካ አገራት ውስጥ የሚገኙ በአስር ሺህ ሔክታሮች የሚገመት ግጦሽ መሬት በአንበጣ መንጋው ወድሟል።
ከጥቂት ወራት በፊት የአንበጣ መንጋው በ350 ስኩዬር ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝን 1.8 ቶን የሚመዝን አረንጓዴ እጸዋትን በአንድ ቀን ውስጥ ይመገባል።
ድርጅቱ እንደሚያምነው አንድ መንጋ ኬንያ ውስጥ 40 ኪ.ሜ በ60 ኪ.ሜ የሚሆን ስፋት ያለውን ቦታ ያካልላል።
አንበጣ ምን ያህል መመገብ ይችላል?
ያደገ የበረሃ አንበጣ በቀን የክብደቱን ያህል መመገብ ይችላል። ይህም ማለት 2 ኪ.ግ ይጠጋል።
ምንጭ፡ FAOበኢትዮጵያና በኬንያ ያጋጠመው ሁለተኛው ዙር የአንበጣ ወረራ ከመጀመሪያው የበለጠ ሲሆን፤ የከሁሉ የሚያሳስበው ደግሞ የተከሰተበት ወቅት ነው ነው ሲሉ የፋኦ ከፍተኛ የአንበጣ ትንበያ ባለሙያ ኪት ክሬስማን ይናገራሉ።
"አሁን በእነዚህ አገራት ወቅቱ ዝናብ የሚጀምርበትና ተክሎች የሚተከሉበት ጊዜ ነው። የተዘራው የሚበቅልበት ጊዜ ቢሆንም የአንበጣ መንጋ ወረራው ደግሞ ተከስቷል።"
አሁን የተከሰተው የአንበጣ መንጋ እያደገ ነው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ እንቁላል በመጣል ሌላ ዙር የአንበጣ መንጋ ምርት በሚሰበሰብበት ጊዜ አድጎ ሰብልን ሊያወድም ይችላል፤ ይላሉ ክሪስማን መንጋው ሁለት ጊዜ የሚያደርሰውን ጉዳት በማሰብ።

የአንበጣ ወረርሽኙ የተከሰተው አገራቱ እየጨመረ ያለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በሚጥሩበትና የእንቅስቃሴ ገደቦችን በጣሉበት ጊዜ ነው።
የ68 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አሊ ቢላ ዋቆ በሰሜን ምሥራቅ ኬንያ አርሶ አደር ሲሆኑ፤ ከረጅም ጊዜ ድርቅ በኋላ በቅርቡ በጣለው ዝናብ ጥሩ ምርት እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገው ነበር።
ነገር ግን የአንበጣው መንጋ የበቆሎና የቦሎቄ ማሳቸውን አውድሞባቸዋል።
"የአንበጣ መንጋው አብዛኛውን ሰብል በልቶ ያወደመው ሲሆን፤ ያልበላው ደግሞ ደርቋል" ይላሉ። "ይህም ከባድ ጉዳት ነው ያደረሰብን። የደረሰውን ሰብል ብናየውም ልንመገበው ግን አልታደልንም።"
በ1960ዎቹ አጋጥሞ የነበረውን የአንበጣ ወረርሽኝ የሚያስታውሱት አሊ ዋቆ፤ በወቅቱ ሰማዩ በአንበጣ ተሸፍኖ ጨልሞ እንደነበረ ይናገራሉ።
"የፀሐይ ብርሐንን ማየት ስለማይቻል ቀኑ ጨልሞ ነበር" ይላሉ።
የአየር ሁኔታ መዛባቱ ደግሞ ያጋጠመውን ችግር አባብሶታል
አሁን ለተከሰተው የአንበጣ መንጋ ምክንያቱ በ2018-2019 ያጋጠመው ከባድ ነፋስና ዝናብ እንደሆነ ይነገራል።
የበረሃ አንበጣ በምዕራብ አፍሪካና በህንድ ውስጥ ባለና 16 ሚሊዮን ስኩዬር ኪ.ሜ በሚሸፍን ደረቅና በረሃማ አካባቢ ውስጥ ይኖራል።
የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው ግን፤ ከሁለት ዓመት በፊት በደቡባዊ የአረብ ልሳነ ምድር ላይ የነበረው እርጥብና አመቺ የአየር ሁኔታ የአንበጣው ሦስት ትውልድ ሳይታወቅ እንዲራባ እድል ፈጥሮለታል።
የአንበጣው ወረርሽን ማሻቀብ የጀመረው ከአንድ ዓመት በ2018 ነበረ

ባለፈው ዓመት መግቢያ ላይ የመጀመሪያው መንጋ ወደ የመን፣ ሳኡዲ አረቢያና ኢራን የሄደ ሲሆን፤ እዚያም የበለጠ ተራብቶ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ተዛምቷል።
ተጨማሪ የአንበጣ መንጋ የተፈጠረ ሲሆን በባለፈው የፈረንጆች ዓመት ማብቂያ ላይ በኤርትራ፣ በጂቡቲና በኬንያ ውስጥም ተከስቷል።

የአንበጣ መንጋው በዚህ ወቅት መራባት በቀጣዮቹ ወራት በምሥራቅ አፍሪካ፣ በየመንና በደቡባዊ ኢራን ውስጥ የበለጠ የአንበጣ ወረራን ይፈጥራል ተብሎ ተሰግቷል።
ምንም እንኳን የአንበጣው መንጋ የተከሰተበት መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ካለው ስፋት የተነሳ ለመከላከል አስቸጋሪ ቢሆንም፤ ክሪስማን እንደሚሉት ግን መንጋው ከመስፋፋቱ በፊት በመጀመሪያው ደረጃ ላይ እያለ የተሻለ የመከላከል ሥራ መስራት ይቻል ነበር።
"ወሳኝ በሆኑት አገራት ውስጥ የአንበጣውን መስፋፋት ለመቆጣጠር ከፍ ያለ ውጤታማ ጥረት ተደርጎ ቢሆን ኖሮ አሁን የሚደርሰውን ጉዳት ይቀንሰው ነበር" ይላሉ።
ግዙፉን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ጥረት ሲደረግ
የአንበጣ መንጋው ካለው ብዛትና ሊያደርስ ከሚችለው ውድመት አንጻር በአፍሪካ ቀንድ አጋጥሞ የማያውቅ በመሆኑ የአካባቢው አገራት ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ነው።
የአንበጣ መንጋ ወረርሽኙን የመቆጣጠሩ ሥራ በሁለት ወሳኝ ተግባራት ላይ የተመሰረተ ነው፤ እነሱም ክትትል ማድረግና ውጤታማ የቁጥጥር ሥራ ማከናወን ናቸው።
በአንበጣ መንጋን ዙሪያ ትንበያ፣ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያና የጊዜ ጥቆማን እንዲሁም የመንጋውን መጠን፣ የሚከሰትበትን ቦታና መራባትን በተመለከተ የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት የሚያቀርበው ‘የበረሃ አንበጣ መረጃ አገልግሎት' ጥቆማን ይሰጣል።
ነገር ግን አሁን አፍሪካ ቀንድ ውስጥ እንዳጋጠመው አይነት የአንበጣ መንጋው ብዛት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከደረሰ ቁጥሩን ለመቀነስና ተጨማሪ መንጋዎች እንዳይፈጠሩና እንዳይዛመቱ አስቸኳይ የመከላከል እርምጃ መወሰድ አለበት።
የአንበጣ መንጋን እንዴት መከላከል ይቻላል?
ምንጭ FAOምንም እንኳን አካባቢን የማይጎደዳና ተፈጥሯዊ አንበጣን የማጥፊያ ዘዴ ለመፈለግ ጥናቶች እየተደረጉ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው የመቆጣጠሪያ ዘዴ የሚረጭ ጸረ ተባይ ነው።
በእጅ በሚያዝ መርጫ፣ በመኪና ወይም በአውሮፕላን ሁሉንም የአንበጣ መንጋ ኢላማ በማድረግ የሚረጨው ጸረ ተባይ ኬሚካል በአንጻራዊ አጭር ጊዜ ውስጥ ነፍሳቱን ይገድላል።
በዚህም ምክንያት ፋኦ በአሁኑ ወቅት ከመንግሥታት ጋር በመተባበር ጸረ አንበጣ መድኃኒት በአውሮፕላን አማካይነት እየረጨ ይገኛል።
"አሁን ያለው አንበጣ እድገቱን የጨረሰ መንጋ በመሆኑ በአውሮፕላን ለሚደረግ የመከላከል ዘመቻ አመቺ ነው። በዚህም የሚያድጉትንና እንቁላል የሚጥሉትን ቁጥር ለመቀነስ ይቻላል።"
ይህ አንበጣውን የመቆጣጠር ሥራ ከወራት በፊት ከነበረው በተሻለ ውጤታማ ነው ይላሉ ክሪስማን፤ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተጣለው የእንቅስቃሴ እገዳ በሥራው ላይ ምንም አይነት እንቅፋትን አለመፍጠሩንም አመልክተዋል።

መሰረተ ልማትና ቀደም ያለ ልምድ ስለማይኖራቸው፤ በተለይ ለበርካታ ዓመታት የአንበጣ መንጋ አጋጥሟቸው ለማያውቁ አገራትና አካባቢዎች ክስተቱ እጅግ አስቸጋሪ ፈተናን ደቅኖባቸዋል።
አሁን በአንበጣ መንጋው ላይ የሚወሰደው እርምጃ ቀጥሎ ምን ሊከሰት እንደሚችል የሚወስን ነው። አሁን የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ተጨማሪ ድንበሮችን በማቋረጥ ሰፊ አካባቢን ካጠቃና በርካታ ሰብልን የሚያወድም ከሆነ፤ "ወረርሽኝ" እንደተከሰተ ሊታወጅ ይችላል።
በዚህም ምክንያት "ሁሉም በመተባበር ዕወቀትና ክህሎትን በመጋራት፤ የአንበጣ መንጋው የበለጠ ጉዳት እንዳያደርስ መከላከል ከተቻለ የከፋ አደጋን መስቀረት ይቻላል" ሲሉ ክሪስማን መክረዋል።
ነገር ግን የትኛውም እርምጃ ለኬንያዊው አርሶ አደር አሊ ቢላ ዋቆና ለቤተሰቡ የዘገየ ነው። እነሱም የአንበጣውን መንጋ ለመከላከል ማድረግ የሚችሉት ነገር ሰብል ላይ ለማረፍ ዝቅ ሲል ጄሪካኖችን በመደብደብና በመጮህ ማባረር ብቻ ነው።
ቢሆንም አርሶ አደር አሊ ቢላ ዋቆ ስለተከሰተው የአንበጣ መንጋ የእራሳቸው ምላሽ አላቸው።
"የሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ይህም የእርሱ ሠራዊት ነው" ይላሉ።
የተሳተፉ
ጽሁፍና ዝግጅት በሉሲ ሮጀርስ፣ የመስክ ዝግጅት በጆይ ኢንዉድ፣ ዲዛይን በዞኢ ባርቶሎሚው እና ሚሊ ዋቺራ፣ ዝግጅት በቤኪ ረሽ፣ በካትሪዮና ሞሪስ እና ፒዩሪቲ ቢሪር። የአንብጣ ምስሎች በስዊድበርት አር ኦት እና ስቴፈን ሮጀርስ እና ጌቲ ኢሜጅስ። የኬንያ እርሻ ቦታ ምስሎች በቢቢሲ።


የምሥራቅ አፍሪካ ፍልሚያ ከአውዳሚው የአንበጣ መንጋ ጋር
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለምሥራቅ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ድጋፍ ጥሪ አቅርቧል
የተባበሩት መንግሥታት ለኢትዮጵያ፣ ለኬንያ፣ ለኤርትራና ለሱዳን የሰጠው ማስጠንቀቂያ