'በማንኛውም ጊዜ ሊገድሉኝ ይችላሉ' በደቡብ አፍሪካ ያሉ ስደተኞች ሰቆቃ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, 'በማንኛውም ጊዜ ሊገድሉኝ ይችላሉ' በደቡብ አፍሪካ ያሉ ስደተኞች ሰቆቃ

በደቡብ አፍሪካ 'መጤ ጠል' በሆኑ የተደራጁ ቡድኖች ተደጋጋሚ ጥቃት ይፈጸማል። አሁንም ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የሄዱ ዜጎች በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ናቸው።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በእንዲህ አይነት ጥቃት የተገደሉ የሌላ አገር ዜጎች ቁጥር ቀደም ሲል ከነበረው በሦስት እጥፍ ጨምሯል። ይህ ቪዲዮ ለደኅንነቱ ሲባል ስሙ ያለተጠቀሰና ምስሉ የማይታይ በደቡብ አፍሪካ የሚገኝ የአንድ ስደተኛን ስጋትና ሰቆቃን ያሳያል።