ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የሚሳኤል ሙከራ የምታደርገው ለምንድን ነው?
ሰሜን ኮሪያ ከአምስት ዓመታት በኋላ የተከለከለውን አህጉር አቋራጭ የተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን ደቡብ ኮሪያና ጃፓን አስታውቀዋል።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆን ኡን በተባበሩት መንግሥታት የተጣለውን ክልከላ በመተላለፍ አዳዲስ የጦር መሳሪያዎች እየሞከሩ ነው።
እነዚህ የሚሳኤል ሙከራዎች በሰሜን ኮሪያ ምጣኔ ሀብት ላይ ጫናን እያስከተሉ ቢሆንም እንደቀጠሉ ናቸው። ለመሆኑ ሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ተዋውሞና ወጪን የሚያስከትልባትን የሚሳኤል ሙከራ የምታደርገው ለምንድን ነው?