የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንታችን እንዳይጠለፍ ምን ማድረግ እንችላለን?
ባለንበት ዘመን የኢሜይ እና የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶቻችን የዕለት ከዕለት ሕይወታችን አካል ናቸው።
እነዚህ የበይነ መረብ መድረኮች በርካታ ግላዊ መረጃዎቻችንን አጭቀው ያያዙ ከመሆናቸው በተጨማሪ ከገንዘብ ዝውውራችን ጋርም ጥብቅ ትስስር አላቸው።
በዚህም ሳቢያ የተለያዩ ጥቅሞችን ለማግኘት የሚፈልጉ የበይነ መረብ ቀበኞች የኢሜይል ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ መለያችንንና የይለፍ ቃላችንን ለማግኘት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ጥረት ያደርጋሉ።
የበይነ መረብ ሰርሳሪዎች (ሃከርስ) እንዴት መረጃዎቻችንን ሰብረው ሊገቡ እንደሚችሉና ይንንም እንዴት መከላከል እንደምንችል ከዚህ ቪዲዮ ይመልከቱ ።