ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ጦርነቱን በመሸሽ ከዩክሬን ለመውጣት የሞከረችው አፍሪካዊት ገጠመኝ
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት መክፈቷን ተከትሎ 1 ሚሊዮን ሰዎች ዩክሬንን ለቀው ወደ ጎረቤት አገራት ሸሽተዋል።
ከዩክሬን ዜጎች በተጨማሪ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ በርካታ አፍሪካውያን ተማሪዎችም ከጦርነቱ ለመራቅ በባቡርና በመኪና ወደ ድንበር አካባቢዎች ለመሄድ ጥረት ቢያደርጉም በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት መድልዎ እንደገጠማቸው ይናገራሉ።
ናይጀሪያዊቷ የህክምና ተማሪ ጄሲካ ኦራክፖ ከዬክሬን ለመውጣት በሚያደርጉት ጥረት አፍሪካውያን በቀለማቸው ምክንያት ችላ ተብለው ለችግር ተጋልጠዋል ትላለች።
እሷም ለሰዓታት በእግሯ ለመጓዝ መገደዷን ትናገራለች።