ስውር ንግድ ስለሚካሄድበት ድብቁ የኢንተርኔት ክፍል ምን ያህል ያውቃሉ?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, በስውር የሚነገድበት የኢንተርኔት ክፍል

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ዘወትር ከምንጠቀመው የኢንተርኔት ክፍል ባሻገር ድብቅ ክፍል እንዳለ ስንቶቻችን እናውቃለን?

በዚህ ስውር የኢንተርኔት ክፍል ከዕፅ አንስቶ አስከ ጦር መሳሪያ የሚነገድበት ሲሆን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንደሆነ ይነገራል። ግብይቱ በቢትኮይን አማካይነት የሚካሄድ በመሆኑ መነሻና መድረሻው እጅግ ውስብስብ ነው።