የቻይናዋ ቤይጂንግ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት መስጠት ጀመረች

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የቻይናዋ ቤይጂንግ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት መስጠት ጀመረች

የቻይናዋ ቤይጂንግ ከተማ ባለሥልጣናት ለመጀመሪያ ጊዜ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጥተዋል። ይህም በርካታ የሮቦት ታክሲዎች በቤይጂንግ ጎዳናዎች ላይ እንዲታዩ አድርጓል።

ለጊዜው አሸከርካሪ አልባ ታክሲዎቹ በመዲናዋ ደቡባዊ ክፍል በ60 ኪሎ ሜትር ውስጥ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል። በሂደት ብዙ ቦታዎች ተደራሽ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰባል።