ሮቦቶችና ሰው ሰራሽ ልህቀት የአምልኮ አገልግሎት ለመስጠት ወደ እምነት ተቋማት እየገቡ ነው
ከተለያዩ ነገሮች ጋር የሚኖረንን መስተጋብር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ/ሰው ሰራሽ ልኅቀት እየቀየረው ነው።
ምግብ፣ የጤና እንክብካቤ፣ ጉዞ እና ሌሎችም የዕለት ከዕለት ፍላጎቶቻችን በዚህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መረዳት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል።
አሁን ደግሞ ሰው ሰራሽ ልኅቀት ወደ አምልኮ ስፍራዎችም እየገባ ለሐይማኖትታዊ ግልጋሎት እየዋለ ነው።
ባለሙያዎች እንደሚሉት ዋና ዋና የሚባሉ ሐይማኖቶች አምልኮን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስለመፈጸም እየመከሩ ነው።
አንዳንዶቹ ቀድመው ይህንን ቴክኖሎጂ ወደ እምነት ስፍራዎቻቸው እንዲገቡ ፈቅደዋል።
የሮቦት ቀሳውስት ይጸልያሉ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓት ያስፈጽማሉ፣ የመንፈስ መታወክ የገጠማቸውን ያጽናናሉ።
ለመሆኑ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአምልኮ ሥርዓታችን ላይ ምን ለውጥ ያመጣ ይሆን?