የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸውን የአፍሪካ አናብስት ለመታደግ ምን ተስፋ አለ?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የአፍሪካ አንበሶች ቀጣይ ተስፋ ይኖራቸው ይሆን?

በአብዛኛው የአፍሪካ ክፍል ውስጥ የሚገኙ አናብስት ቁጥራቸው ተመናምኖ ህልውናቸው አደጋ ላይ ወድቋል።

በዚህም ሳቢያ በአህጉሪቱ የነበረው የአናብስት መንጋ በ95 በመቶ የቀነሰ ሲሆን በ25 የአፍሪካ አገራት ደግሞ የአንበሳ ዘር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መመጥፋቱ እተነገረ ነው።

እነዚህን የዱር እንስሳት ከፍጹም ጥፋት ለመታደግ በአንዳንድ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ጥረት እየተደረገ ነው። ለዚህ ደግሞ አናብስቱ በሚኖሩበት አቅራቢያ ያሉ ማኅበረሰቦችን በማሳተፍ የሚደረገው ጥበቃ እንደዋነኛ አማራጭ እየታየ ነው።

በእርግጥ ይህ ማኅበረሰብ ተኮር ጥበቃ አናብስቱን ከመጥፋት ይታደጋቸው ይሆን? በዚህ ዙሪያ የምትሰራው ዶ/ር ሞሪንጌልስ ም'ቢዛህ ተስፋ መኖሩን ታብራራለች።