ከ116 ሚሊዮን በላይ የቲክቶክ ተከታይ ያለው የካቢ ላሜ ስኬት ምስጢር ምንድን ነው?
የ21 ዓመቱ ሴኔጋላዊ፣ ቲክ ቶክ ላይ ዝናው ናኝቷል፤ እጅግ በጣም ተወዳጅ ሆኗል፤ በመላው ዓለም ከ116 ሚሊዮን በላይ ተከታይም አፍርቷል።
ይህም በዓለም ላይ ስመጥር ከሆኑ ሰዎች ጋር በጥምረት የመስራት እድልን ፈጥሮለታል። ከእነዚህም መካከል ናኦሚ ካምቤል እና ግሬታ ተንበርግ ይገኙበታል።
በቲክቶክ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተከታይ ያለው ሁለተኛው ሰው የሆነው ካቤ፣ ለዚህ ስኬት ያበቃው ምን ይሆን?