ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ ሚሳኤል የምታስወነጭፈው ለምንድን ነው?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ ሚሳኤል የምታስወነጭፈው ለምንድን ነው?

ሰሜን ኮሪያ በቴክኖሎጅ የተራቀቀ አዲስ ሚሳኤል አስወንጭፋለች።

ይህ ሚሳኤል በሚተኮስበት ወቅት የአቅጣጫ መቀየሪያ የተገጠመለት ሲሆን ጠላት ለመከላከል የሚያደርገውን ሙከራ ማምለጥ የሚችል ነው።

ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ የሞከረችው ሚሳኤል በአንድ ወር ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የተደረገ ነው።

የዓለም አቀፉ ውግዘት እንዳለ ሆኖ ሰሜን ኮሪያ ግን ሚሳኤል ማስወንጨፏን እንደቀጠለች ናት።

አንዳንዶቹ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የውሳኔ ሃሳብ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው ጥብቅ ማዕቀብም አስከትለውባታል።