ቀነኒሳ ያሳበውን ያላሳከው በጤና እና በአየር ንብረት ምክንያት ነው አለ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ቀነኒሳ ያሳበውን ያላሳከው በጤና እና በአየር ንብረት ምክንያት ነው አለ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በበርሊን ማራቶን ቀድሞ ያሰበውን ሳያሳከው የቀረው በጤና ጉዳይ እና በአየር ንብረት ምክንያት መሆኑን ተናገረ።

አትሌት ቀነኒሳ ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰነን ለመስበር አቅዶ የነበረ ቢሆንም ውድድሩን ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ከውድድሩ በኋላ ቀነኒሳ ለቢቢሲ እንደገለጸው ትናንት በበርሊን ከተማ የነበረው የአየር ሞቃታመ በመሆኑ ውድድሩ በተፈለገው ፍጥነት መሄድ አልቻለም ብሏል።

"ከስምንት ወር በፊት በኮቪድ ታምሜ ነበር" ያለው አትሌት ቀነኒሳ፤ በሕመሙ ምክንያት ለአንድ ወር ያክል ልምምድ ሳያደርግ መቆየቱ ያሰበውን እንዳያሳካ እንዳደረገው ተናግሯል።