በኢትዮጵያ የተደረገው የመጀመሪያው ተደራራቢ የልብ ቀዶ ህክምና
የ55 ዓመት ጎልማሳ ተደራራቢ የልብ ሕመም ገጥሟቸው ወደ ሕክምና ተቋም ሲያመሩ በአገር ውስጥ የቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ይከናወናል ብለው ያሰቡ አይመስሉም። ዶ/ር ፈቃዱ አግዋር እና አስር ባልደረቦቻቸው የተሳተፉበት ቀዶ ጥገና ስድስት ሰዓት የፈጀ ሲሆን፣ የአዛውንቱን ጤናም ወደ ነበረበት መመለስ አስችሏል። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለው ቀዶ ጥገና እንዴት ተከናወነ?