ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በዩኒቨርስቲ ውስጥ የአማርኛ ቋንቋን የምታስተምረው ቻይናዊት
ጃንግ ቹንጋይ ትባላለች። ቻይናዊት ናት። እርሷ ግን "ግማሽ ኢትዮጵያዊ ነኝ" ነው የምትለው። በአባቷ አሊያም በእናቷ ኢትዮጵያዊ ሆና ወይንም የኢትዮጵያ ደም ኖሮባት አይደለም። አማርኛ ቋንቋ በመቻሏ እንጂ።
ንግግራችንን ለመቀጠል 'ቹንጋይ' ስል ጠራኋት። "ፀደይ ብለሽ ጥሪኝ" አለችኝ- ፀደይ ጃንግ።