ምርጫ 2013፡ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ለኢትዮጵያና ለአካባቢው አገራት ምን ይዞ ይመጣል?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የኢትዮጵያ ምርጫ በአካባቢው አገራት ላይ ምን ውጤትን ያስከትላል?

የኢትዮጵያ ምርጫ በአካባቢው አገራት ላይ ምን ውጤትን ያስከትላል? በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ምርጫ በተመለከተ የተለያዩ ሃሳቦች ይሰነዘራሉ። አንዳንዶች ምርጫው አገሪቱ ወደፊት ለመገንባት ላሰበችው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረት የሚጥል ነው ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ ከምርጫው ይልቅ ሁሉን አቀፍ አገራዊ ውይይት መደረግ ነበረበት ይላሉ።

ከምርጫው በኋላ የሚኖሩት ክስተቶች ከኢትዮጵያ ባሻገር በዙሪያዋ ባሉ አገራት ላይ የእራሳቸው የሆነ ውጤት እንደሚኖራቸው ግን ሁሉም ይስማማሉ።