'ወይ ያልፍልናል ወይ እናልፋለን' ኢትዮጵያውያን ስደተኞች

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, 'ወይ ያልፍልናል ወይ እናልፋለን' የአረብ አገር ስደተኞች

በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሳዑዲ አረቢያ ለመድረስ ጦርነት፣ ተራራ፣ በረሃ የበዛባቸውን አካባቢዎችንና ቀይ ባሕርን ጨምሮ በእግር እና በጀልባ ይጓዛሉ።

አብዛኞቹ በውሃ ጥም እና ረሃብ ክፉኛ ይጎዳሉ፤ አለፍ ሲሊም ሕይወታቸው እያለፈ በየመንገዱ አሸዋ ላይ የሚቀበሩት ጥቂት አይደሉም።

ቀይ ባሕርን ከተሻገሩ በኋላ ደግሞ በየመን ደላሎች እየተጠለፉ ለወራት አንዳንዴም ለዓመታት ማስለቀቂያ ገንዘብ አምጡ እየተባሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ይገረፋሉ።

ቢቢሲ በእንደዚህ አይነት ያለፉ ባለታሪኮችን አነጋግሯል።