ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ፡ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊን ታንዛኒያውያን በምን ያስታውሷቸዋል?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊን ታንዛኒያውያን በምን ያስታውሷቸዋል?

'ቡልዶዘር' የተባሉት የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ በ54 ዓመታት የታንዛኒያ የነጻነት ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የነጻነት ቀን እንዳይከበር ያደረጉት እሳቸው ናቸው። "ቸበርቻቻ አያስፈልግም ሥራ ነው እንጂ" አሉ።

"ሕዝቤ ሆይ! ነጻ የምትወጣው የነጻነት በዓልን በማክበር ሳይሆን ተግቶ በመሥራት ነው፤ ስለዚህ እጅህ መቁሸሽ አለበት" ሲሉ ጮኹ።

ማጉፉሉ ሕዝቡን በማዘዝ ወደ ቅንጡ ቤተ መንግሥት የሚገቡ ሰው አልነበሩም። እሳቸውም በዘመቻ ይሳተፉ ነበር። ሠርተው ያሳያሉ። ሌሎችም ብዙ አስገራሚ ነገሮች አሏቸው። የተወሰኑትን በእዚህ መልኩ አዘጋጅተናቸዋል።