የቢራቢሮ እርባታ በኬንያ በሳምንት 150 ዶላር እያስገኘ ነው
በኬንያ የባህር ዳርቻዎች አካባቢ የቢራቢሮ እርባታ ሁነኛ የገቢ ማስገኛ እየሆነ ነው።
በርካታ ገበሬዎች ቢራቢሮ በማርባት ኑሯቸውን እየመሩ ነው ተብሏል። ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ ስርጭት ገበያው ላይ ተፅዕኖ ቢያሳድርም ገበያው ሲደራ ግን ገበሬዎቹ ከቢራቢሮ ሽያጭ በሳምንት ከ 150 ዶላር (6,000 ብር ገደማ) በላይ ገቢ እንደሚያገኙ ይናገራሉ።
አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና ቱርክ ቢራቢሮዎችን በቀዳሚነት የሚገዙ አገራት ናቸው።