አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማን ናቸው?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ማን ናቸው?

በአሜሪካ ታሪክ እጅግ አወዛጋቢ ከሆነው የ2020 ምርጫ በኋላ ጆ ባይደን አሸናፊ መሆናቸው ተረጋግጧል። ነገር ግን ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በፖለቲካ ውስጥ የቆዩት፣ ብዙ ውድቀትና ስኬቶችን ያስተናገዱት እና በግል ሕይወታቸው አሳዛኝ ገጠመኞችን ያስተናገዱት የጆ ባይደን ሕያወት ምን ይመስላል?