የኮሮናቫይረስ ክትባት በፍጥነት ዝግጁ የሆነበት ሂደት

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የኮሮናቫይረስ ክትባት ዝግጁ የሚሆነው መቼ ነው?

ሕዳር ወር ላይ ፋይዘር እና ሞደርና የተሰኙ ክትባት አምራች ኩባንያዎች ከ90 በመቶ በላይ ውጤታማ የሆነ ክትባት አበልጽገዋል።

ሕይወትን ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ለመመለስ ፈዋሽ መድሃኒት እስካልተገኘ ድረስ ክትባት ወሳኝ ሚና አለው። ተመራማሪዎችም ምርምራቸውን የጀመሩት ባለፈው ዓመት ሲሆን አሁን ሥራቸውን በማጠናቀቅ ላይ ናቸው። ሥራው በፍጥነት መጠናቀቁን ተመራማሪዎች ይናገራሉ።