የእግር ኳሱ ዓለም ሐዘን በአርጀንቲናዊው ኮከብ ዲያጎ ማራዶና ሞት
የእግር ኳሱ ዓለም በአርጀንቲናዊው ኮከብ ድንገተኛ ሞት ሐዘን ውስጥ ገብቷል። ማራዶናን በተጫጨችነትም ሆነ በአሰልጣኝነት ዘመኑ የሚያውቁት ሰዎች ለቢቢሲ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
የሊቨፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ "እንኳን ጨዋታው ሲያሟሙቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴም ልዩ ነው" ብለውታል። የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ፈረንሳያዊው ዚነዲን ዚዳን ደግሞ "በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የዓለማችን ወጣቶች አርዓያ መሆኑን የመንገር ዕድሉ ገጥሞኝ ነበር" ይላል።