ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አካል ጉዳተኛ መሆኗ ሌሎችን ከመርዳት ያላገዳት ሜሮን ተስፋይ
ሜሮን ተስፋይ ከልጅነቷ ጀምሮ የነርቭ ችግር ገጥሟት ሙሉ የሰውነት ክፍሏን ማዘዝ አትችልም።
በዚህ ሁኔታ ሆና እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ድረስ ትምህርቷን ተከታትላላች። ሌሎችን ማገዝ ዓላማዋ ያደረገችው ሜሮን፣ አይነ ስውራን ሆቴል ቤት ሂደው ለመስተናገድ እንዳይቸገሩ የሚያግዝ የብሬል የምግብ ዝርዝር ማውጫ (ሜኑ) አዘጋጅታለች።
የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ የሚገጠም ብሬልም ሰርታ አይነ ስውራንን እንዲያግዝ አድርጋለች።