ደራሲ፡ ለቡከር ሽልማት የታጨችው ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ
ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ሴት የነፃነት ታጋዮችን በሚዘክረው 'ዘ ሻዶው ኪንግ' መፅሃፏ ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ ለቡከር ሽልማት እጩዎች መካከል አንዷ ሆናለች።
ለነፃነት በተደረገው ትግል ላይ የጥቂት ወንዶች ሚና በጎላበት ሁኔታ ሴት ነፃነት ታጋዮች ከታሪክ መዝገብ መፋቃቸውንና ግዙፍ አስተዋፅኦቸው ምን ይመስል ነበር በማለት አስርት አመታትን ወደ ኋላ ተጉዛም መዓዛ በ'ዘ ሻዶው ኪንግ' ታስቃኛለች።