ኮሮናቫይረስ፡ "በበሽታው በመያዜ ከህመሙ በላይ ጭንቀቱ በርትቶብኝ ነበር" - ዶ/ር ፋሲካ አምደሥላሴ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, በጭንቀት ምክንያት መሞቴ እና መትረፌ አጠራጥሮኝ ነበር፡ ዶ/ር ፋሲካ አምደስላሴ

በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ሳይንስ ት/ቤት ዲን እና የቀዶ ሕክምና ሐኪሙ ዶ/ር ፋሲካ አምደሥላሴ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ሁለት ሳምንታትን በሕክምና ማቆያ ውስጥ አሳልፈዋል።

አሁን ከህመማቸው አገግመው ወደ ዕለት ተዕለት ሥራቸው ተመልሰዋል። በሕክምና ላይ እያሉ በሽታው አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንደምሞት ወይም እንደምተርፍ መለየት ተስኖኝ ጭንቀት ውስጥ ገብቼ ነበር ይላሉ።