ስደት፡ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች
በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳኡዲ አረቢያ ችግር ላይ ናቸው። ብዙ ቁጥር ያላቸው ሴት ስደተኞች ውሃ በሞላው ጠባብ ክፍል ውስጥ ታስረው ድረሱልን እያሉ ነው።
ወንዶች ደግሞ ከፍተኛ ሙቀት ባለበት አካባቢ እጅግ በተጨናነቀ ሁኔታ ተፋፍገው በመተኛት ለቆዳ በሽታ እየተጋለጡ ነው። በተደጋጋሚ የድረሱልን ጥሪ ቢያቀርቡም እስካሁን ግን ምላሽ አላገኙም። ሂውማን ራይትስ ዎች በስፍራው በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ የቃኘበት ምስል በዚህ መልኩ ተቀናብሯል።