ከሊባኖስ ፍንዳታ የተረፈ፡ "በቅጽበት መስማት አቃተኝ"

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ከሊባኖስ ፍንዳታ የተረፈ፡ "በቅጽበት መስማት ተስኖኝ ነበር"

በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ማክሰኞ ዕለት ባጋጠመው ከባድ ፍንዳታ ከ130 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። ከአደጋው የተረፉ ሰዎች የነበረውን ሁኔታ ለቢቢሲ አስረድተዋል።

በወቅቱ ቃለ መጠይቅ እያደረገች የነበረችው የቢቢሲዋ ጋዜጠኛ መጠነኛ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን ከዚህ ከባድ አደጋ በህይወት ከተረፉት ሰዎች መካከል አንዷ ናት።