የቤይሩቱ ፍንዳታ በብዙ ርቀት ላይ የሚገኙ ህንጻዎችን አውድሟል

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የቤሩት ፍንዳታ በብዙ ርቀት ላይ የሚገኙ ህንጻዎችን አውድሟል

የሌባኖሷ ቤይሩት በከፍተኛ ፍንዳታ ተናወጠች።

የቀድሞ የሌባኖስ ጠቅላይ ሚንስትር ራፊክ ሃሪሪ ላይ ግድያ ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች ላይ የፊታችን ዓርብ ብይን ለመስጠት የተዘጋጀችው የሌባኖስ መዲና ቤይሩት በከፍተኛ ፍንዳታ መናወጧ ተነገረ።

እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ፍንዳታው የተሰማው የከተማዋ ወደብ የሚገኝበት አቅራቢያ ነው። ምንም እንኳ እስካሁን ማረጋገጫ ባይገኝም ሁለተኛ ፍንዳታ መሰማቱም ተነግሯል።