"ልጄ የሞተው ለእውነት ነው" የሃጫሉ አባት

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, "ልጄ የሞተው ለእውነት ነው"

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ ድፍን አንድ ወር ሆኖታል።

የሃጫሉ ግድያ ሚሊዮኖችን አስደንግጧል፤ በርካቶችን አስቆጥቷል፤ አሳዝኗል። ግድያውን ተከትሎም በተነሳ አለመረጋጋት ከ167 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቤት ንብረታቸው ዶግ አመድ ሆኗል።

የሃጫሉ ህልፈት ዛሬም ድረስ ለወላጅ አባቱ መራር ነው። አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ስለ ልጃቸው ሲናገሩ፤ "ውሸት አይወድም። እውነት ነው የሚወደው፤ የሞተውም ለእውነት ነው" ይላሉ

አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ልጃቸውን ሲያስታውሱ "ልጄ ጀግና ነው። ለእውነት ይሞታል" ይላሉ።

"ሃጫሉ ከልጅነቱ ጀምሮ ጀግና እና ደፋር ነበረ። ውሸት አይወድም። እውነት ነው የሚወደው፤ የሚሞተውም ለእውነት ነው" የሚሉት የሃጫሉ ወላጅ አባት አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ፤ ሃጫሉ ለሞት የተዳረገው ለወገኑ በመቆርቆሩ እና "ያገባኛል" በማለቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

"እኔ የሚያበሳጨኝ ነገር ሃጫሉ እንደእሱ ጀግና በሆነ ሰው ሳይሆን በገንዘብ በተገዙ ፈሪዎች መንገድ ላይ መቅረቱ ነው" ሲሉም ያክላሉ።