ኮሮናቫይረስ፡ ወርሃዊ ገቢያችን ከ15 ሺህ ብር ወደ ዜሮ ወርዷል፡ በላሊበላ የሚገኝ አስጎብኚ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ወርሃዊ ገቢያችን ከ15 ሺህ ብር ወደ ዜሮ ወርዷል፡ የላሊበላ አስጎብኚ

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴን በመገደቡ ቱሪስቶች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው የቱሪዝም መዳረሻዎችን መጎብኘት አልቻሉም። ቱሪዝምን የገቢ ምንጫቸው አድርገው የሚኖሩ ተቋማትና ግለሰቦችም በዚሁ ምክንያት ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ድቀት እየደረሰባቸው ነው። በዚህ ረገድ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ነዋሪዎቿ በቱሪዝምና ከቱሪዝም ጋር ተያይዘው በሚመጡ ግብይቶች ኑሯቸውን የሚመሩባት የላሊበላ ከተማ ቀዳሚ ተጠቃሽ ነች። በከተማዋ ለዘጠኝ ዓመታት በአስጎብኝነት ተሰማርቶ ይሰራ የነበረው አያሌው ሰጠኝም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ወርሃዊ ገቢው ከ15 ሺህ ብር ወደ ምንም መቀነሱን ነግሮናል።