በመካከለኛው ምሥራቅ ኮሮናቫይረስን አሰራጭቷል የተባለው አየር መንገድ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ለመካከለኛው ምስራቅ ኮሮናቫይረስን ያከፋፈለው አየር መንገድ

ከኢራን የሚነሳ አንድ አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ ተደጋጋሚ በረራዎችን ያደርግ ነበር ተብሎ ይከሰሳል። ይህ አየር መንገድ ኢራን ውስጥ የሚገኝ የግል አየር መንገድ ሲሆን የተጣሉት እገዳዎች ሳይገድቡት ወደ ተለያዩ አገራት በመብረር ለኮሮናቫይረስ ስርጭት አስተዋጽዖ ማድረጉ ይነገራል።

ይህ አየር መንገድ መሃን አየር መንገድ ይባላል። አየር መንገዱ ከታላቁ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ቁርኝት ስላለው ምናልባትም ደጀን ያደረገው የአብዮታዊ ዘቡን ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው።