ኮሮናቫይረስ፡ በኮቪድ-19 ዙሪያ የሚለቀቁ ሐሰተኛ መረጃዎችን እንዴት መለየት ይቻላል?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, በኮሮናቫይረስ ዙሪያ የሚለቀቁ ሐሰተኛ መረጃዎችን እንዴት መለየት ይቻላል?

የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ የሚፈበረኩ ሐሰተኛ መረጃዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በህንድ የበሽታው መድሃኒት ተገኘ ተብሎ ሰዎች የላም ሽንት ጠጥተዋል፤ እበት ላይም ተንከባለዋል። በተመሳሳይ ኢራን ውስጥ ያልተገባን ነገር መድሐኒት ነው በሚል የተሰራጨውን ሐሰተኛ መረጃ እውነት አድርገው በመቀበል ባዕድ ነገር ጠጥተው ከ300 በላይ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል። በኢትዮጵያም ጉዳታቸው ከፍተኛ ባይሆንም ሐሰተኛ መረጃዎች ሲሰራጩ ይስተዋላል። ለመሆኑ እነዚህን ሐሰተኛ መረጃዎች እንዴት መለየት ይቻላል?